በትናንትናው የአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ቶተንሀም የመጀመሪያ 3 ነጥቡን ሬድ ስታር ቤልግሬድ ላይ 5 ጎሎችን በማስቆጠር አግኝቷል። ለ ቶተንሀም ጎሎቹን  ሃሪ ኬን(2), ሰን(2) እና ላሜላ አስቆጥረዋል።

 

ትላልቆቹ ቡድኖች 3 ነጥብ ባሳኩበት ምሽት ሪያል ማድሪድ ቶኒ ክሩስ ባስቆጠራት የ18 ደቂቃ ጎል ጋላታሳራይን 1-0 አሸንፈዋቸዋል።

ማንቸስተር ሲቲ የጣልያኑን አታላንታ አስተናግዶ 5 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፉዋል። ኢትሃድ ላይ በተደረገው ጨዋታ ራሂም ስተርሊንግ ሃትሪክ የሰራ ሲሆን አርጀንቲናዊው ሰርጂዮ አጉየሮ 2 ጎሎችን አስቆጥሩዋል።

የ ፓውሎ ዲያባላ ድንቅ ብቃት በታየበት የ ዩቬንቱስ እና ሎኮሞቲቭ ሞስኮ ጨዋታ ዩቬንቱስ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፉዋል። ጎሎቹን ዲያባላ አስቆጥሩዋል።

 

በሌሎች ጨዋታዎች

አትሌቲኮ ማድሪድ 1-0 ሌቨርጉሰን

ሻካታር ዶኔስክ 2-2 ዳይናሞ ዛግሬብ

ኦሎምፒያኮስ 2-3 ባየር ሙኒክ

ክለብ ብሩጅ 0-5 ፒኤስጂ

 

በሚካኤል ደመወዝ

የ ፌስቡክ ገዓችንን ላይክ ያርጉ        https://www.facebook.com/ethiopiansportesp/
የ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ      https://t.me/ethiopiansport12