የማንቸስተር የውጤት አልባ ጉዞው አሁንም ሲቀጥል ከኤዜድ አልካማር ጋር ያለ ግብ በአቻ ውጤት ጨርሷል።

ሌላው የእንግሊዝ ክለብ አርሰናል በታዳጊ ተጨዋቾቹ ደምቆ አምሽቷል ስታንዳርድሌጅን 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል። ለአርሰናል ጎሎቹን ወጣቱ ብራዚላዊ ተስፈኛ ጋብራኤል ማርቲኔሊ(13′, 16′), ጆ ዊሎክ(22′) እና ዳኒ ሴባዮስ(57′) አስቆጥረዋል። በዚህ ጨዋታ የ ሜሱት ኦዚል ከቡድኑ ውጪ መሆኑ ብዙዎችን ቢያስቆጣም የ ሄክቶር ቤሌሪን እና የ ኬረን ቴርንኒ መሰለፍ በአሰናል ቤት አዲስ ተስፋ ሆንዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች

ቤሽኪታሽ 0-1 ዎልቭስ
ያንግ ቦይስ 2-1 ሬንጀርስ
ሴልቲክ 2-0 ክሉጅ
ሲቪያ 1-0 አፖል ኒኮሲያ
ሉጋን 0-0 ዳይናሞ ኬቭ
ማልሞ 1-1 ኮፐንሀገን
ሮዘንበርግ 1-4 ፒኤስቪ
ላዚዬ 2-1 ሬንስ
ፌኖርድ 2-0 ፖርቶ
ሲኤስኬ ሞስኮ 0-2 ኢስፓኖል
ሴንት ኢቴን 1-1 ዎልፍስበርግ

በሚካኤል ደመወዝ