የአውሮፓ በቻምፒየንስ ሊግ ትናንት በተደረጉ ጨዋታዎች ቶተንሀም ሆትስፐርስ ባልተጠበቀ ሁኔታ በባየርሙኒክ 7 ጎሎች ተቆጥሮበት 7-2 በሆነ ሰፊ ውጤት ተሸንፏል በጨዋታዉ ኮኮብ የነበረው የቀድሞው የአርሰናል ተጫዋች ሰርጂ ግናብሪ 4 ጎሎችን አስቆጥሯል።ከጨዋታው በኋላ የቶቴንሃሙ አሰልጣኝ ማውሪስዬ ፖቼትኖ ውጤቱ እንዳበሳጫቸው እና የባየርን ሙኒኮች የአጨራረስ ብቃት አድንቀዋል።

በሌላ ጨዋታ ሪያል ማድሪድ ከመመራት ተነስተው በሜዳቸው ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።

በሌሎች ጨዋታዎች
Galatasaray 0-1 Paris Saint-Germain
Fk Crevna Zvezda 3-1 Olimpiacos
Atalanta 1-2 shakatar donetsk
Juventus 3-0 Bayer leverkusun
Manchester city 2-0 Dynamo zagreb
Locomotive Moskva 0-2 Atletico Madrid

በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ሁለተኛ ዙር የምድብ ጨዋታዎች ዛሬ ሲቀጥል

በዛሬው ተጠባቂ ጨዋታ ባርሴሎና በዚህ አመት በሴሪ ኤ ሽንፈት ያልገጠመውን የአንቶንዬ ኮንቴን ኢንተር ሚላንን ያስተናግዳል።

በሌላ ጨዋታ ሊቨርፑል የአመቱን የቻምፒዮንስ ሊግ ሙሉ 3 ነጥብ ለማግኘት በሜዳው ሳልስበርግን ያስተናግዳል።

በሌሎች ጨዋታዎች
Genk vs Napoli
Slavia Prague vs Borussia Dortmund
Leipzig vs Lyon
Zenit st Petersburg vs Benfica
Lille vs Chelsea
Valencia vs Ajax

በሚኪ