በቀድሞ ታሪካቸው ማደር የተሳናቸው ማንቺስተር ዩናይትድ እና አርሰናል የሳምንቱን መዝጊያ ጨዋታ ሰኞ ከምሽቱ አራት ሰዓት ላይ በኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም ያካሂዳሉ፡፡

ማንቺስተር ዩናይትድ በክረምቱ የተከላካየች ሪከርድ በሆነ ሂሳብ ሀሪ ማጓየር እና አሮን ዋንቢሳካ በማስፈረም እንዲሁም በርካቶች ከአለማችን ምርጥ ግብ ጠባቂዎች ተርታ የሚመደውን ዴቪድ ዴሂያን ቢይዝም አሁንም ጎሎችን ማስተናገዱን ቀጥሎበታል፡፡

በተለይ ደግሞ የመሐል ሜዳው ነገር ከጊዜ ወደጊዜ ጨዋታን በፍፁም መቆጣጠር እየተሳነው መሄዱ በሰኞው ጨዋታ ጎንዱዚን እና ሴባሊዮሽን በያዘው የአርሰናል የመሀል ሜዳ የበላይነት ተወስዶበት ለሽንፈት ሊዳርገው እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም የማርከስ ራሽፎርድ ለሁለት ሳምንታት ከሜዳ መራቅ እና የአንቶኒ ማርሻል ለጨዋታው የመድረሱ ነገር አጠራጣሪ መሆን አሁንም ክለቡ በታዳጊዎቹ ማሰን ግሪንዉድ እና ዳንኤል ጄምስ ላይ የጎል የማግኘት ተስፋውን አድርጓል፡፡

የዩናይትድ አለቆች ክረምቱን በተለይ በአካል ብቃት እና ፊትነስ ጋር የተያያዘ ጠንካራ ዝግጅት ስናደርግ ነበር ቢሉም አሁንም በጉዳት መታመሱን ቀጥሏል፤ በጨዋታው ማንቸስተሮች ለረጅም ጊዜ በጉዳት ከራቁት ኤሪክ ቤሊ እና ፎንሱ ሜንሳህን በተጨማሪ ማርከስ ራሽፎርድን አገልግሎት የማያገኙ ሲሆን አንቶኒ ማርሻል እና ሉክ ሾው መድረስም አጠራጣሪ ሆኗል፡፡

በሌላ በኩል ግን በሳምንቱ አጋማሽ መጫወት የቻለውን ፖል ፖግባን በፕሪሚየር ሊጉ መልሶ ያገኛል፡፡

በአርሰናል በኩል የተከላላይ መስመሩ አሁንም ደካማው ጎን ሆኖ የሚቀጥል ይመስላል፤ ነገር ግን በሳምንቱ አጋማሽ ከጉዳት ተመልሶ የተሻለ ብቃት ያሳየው ሮብ ሆልዲንግ በጨዋታው ቋሚ አሰላለፍ ውስጥ የሚካተት ከሆነ የተሻለ ያደርገዋል ተብሎ ይገመታል በተጨማሪም የማንቺስተር ዩናይትድ አጥቂ ክፍል ደካማ መሆን ፈተናቸውን ያቀለዋል፡፡

በአርሰናል በኩል መልካሙ ዜና የመሐል ሜዳው የተሻለ አማራጭ እና አደረጃጀት የያዘ መሆን ለጨዋታው ቁልፍ ሚና ይጫወታል ተብሎ ይገመታል፤ በተለይ ደግሞ በቅርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ ለፈረንሳይ ብሄራዊ ቡድን ጥሪ ደርሶት የነበረው ጎንዱዚን እና ስፔናዊው ሴባሊዮሽን ከተጋጣሚያቸው ላይ ብልጫቸውን ለመውሰድ ወሳኝ ናቸው፡፡

እንዲሁም እንደሰሞንኛ አቋሙ ሁሉ ቡካዮ ሳካ ድንቅ ብቃቱ ይጠበቃል፡፡
አርሰናል ስሚዝ ሮው፣ ላካዜት እና ማቭሮፓኖስን በጉዳት ምክንያት እንዲሁም ሜትላንድ ናይልስ ከአስቶንቪላ ጋር ባገኘው ቀይ ካርድ ምክንያት ለጨዋታው የማይጠቀም ሲሆን ሮብ ሆልዲንግ፣ አዲስ ፈራሚው ኬረን ቴርኒ እና ሄክቶር ቤለሪን ግልጋሎት አሰልጣኙ ካመኑ መድፈኞቹ ማግኘት ይችላሉ፡፡

ከጨዋታው መሐል ፡-በዩናይትድ ቤት
በማንቺስተር ዩናይትድ አዲስ የተሰማ ዜና ቢኖር በተጫዋቾች እና በአልጣኝ ኦሊጎናር ሶልሻየር መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ነው፡፡ 
በተለይ በሳምንቱ አጋማሽ በካራባኦ ካፕ ከሮችዴል ጋር ተገናኝተው በፍጹም ቅጣት ምት ባሸነፉበት ጨዋታ ፖል ፖግባን ጨምሮ ሌሎች ልምድ ያላቸው ተጫዋቾች በመጀመሪያው አሰላለፍ ውስጥ ቢኖሩም የ21 አመቱን እንግሊዛዊ አሌክስ ተንዝቢን አምበል አድርጎ መጠቀሙ ለነገሩ መጠናከር አስተዋፅዖ አድርጓል፡፡

ይህም ነገር እየከረረ የሚሄድ ከሆነ ከወዲሁ ስሙ ከአርሰን ቬንገር እና ማውሪዚዮ ፖሸቲኖ ጋር እየተያያዘ በሚገኘው ክለብ የአሰልጣኝ ኦሊጎናር ሶልሻየር መቆየት አጠራጣሪ ይሆናል፡፡

ከጨዋታው መሐል ፡ በአርሰናል ቤት አዲስ የተሰማው ዜና አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ተጫዋቾቻቸውን አንበላቸውን እንዲመርጡ መጠየቃቸው ነው፡፡
ክለቡ ሎረንት ኮሸንሊ፣ ፒተር ቼክ እና አሮን ራምሴ ጋር ከተለያየ በኋላ ቋሚ አንበል የሌለው ሲሆን እስከ አሁን ባሉት የሊጉ ጨዋታዎች ላይ ቡድኑን በአምበልነት የመራው ግራኒት ዣካ አሁንም ከሌሎቹ የተሻለ እድል እንዳለው የሚጠበቅ ሲሆን አዲስ ፈራሚው ዴቪድ ሊዊስ፣ ሮብ ሆልዲንግ ፣ ሜሱት ኦዚል፣ ኦቦሚያንግ እና ላካዜቴ ሌሎች ተፎካካሪዎች ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ አሰልጣኝ ኡናይ ኤምሬ ግን ከዋናው አንበል በተጨማሪ ሌሎች አራት ምክትሎች እንዲኖር እንደሚፈልጉ ተነግሯል፡፡
ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አሰላለፍ
ማንቸስተር ዩናይትድ፡- ዴሂያ፣ ዋን ቢሳካ፣ ሊንደሎፍ፣ ማጓየር፣ ያንግ፣ ማክቶሚናይ፣ ፖግባ፣ ጄምስ፣ ማታ፣ ግሪንዉድ፣ ሊንጋርድ
አርሰናል ፡- ሌኖ፣ ቻምበርስ፣ ሉዊዝ፣ ሶክራተስ፣ ቴረኒ ፣ ዣካ፣ ጎንዱዚ፣ ሴባሊዮስ፣ ሳካ፣ ፔፔ፣ ኦቦሚያንግ ናቸው።