ቫን ዳይክ የ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የምንግዚም ትልቁ ተከላካይ ተደርጎ ሊቆጠር የማይችልበት ቁልፍ ምክንያት ።

በማንችስተር ሲቲ የተካሄደው የቪሰነት ኮምፓኒ የመሸኛ ጨዋታ ከኤቲሃድ ውጭ አዲስ ሐውልት መሰራቱን፣ ካምፓኒ በጭን ጉዳት ምክያት ከጨዋታው ውጪ መሆኑን ጨምሮ ጥቂት አርዕስቶች ፈጥሩዋል ፡፡ ነገር ግን ካምፓኒ ቫን ዳይክ ላይ የሰጠው አስተያየት የበለጠ ትኩረት አጊንትዋል ፡፡

ከፕሪሚየር ሊጉ ታላላቅ ተከላካዮች አንዱ የሆነው ኮምፓኒ ፣ የፕሪሚየር ሊጉ ታላቅ ማነው ለሚለው ጥያቄ “እኔ ወደ ቫን ዳይክ አመጣዋለሁ” ነበር መልሱ ፡፡

የሊቨርፑሉ የሁዋላ ደጀን ከፋቢዮ ካናቫሮ ቀጥሎ ለመጀመሪያ ጊዜ የ UEFA የዓመቱ ምርጥ ተጨዋች ሆንዋል ግን እሱ በእርግጥ የፕሪሚየር ሊጉ የምንግዚም ታላቁ ተከላካይ ነው??

ምንም እንኩዋን ያለ ቫን ዳይክ ሊቨርፑል በማድሪድ ለስድስተኛ ጊዜ የሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ አሸናፊ እንደማይሆን ቢታሰብም ይህ ዋንጫ ለቫን ዳይክ በ 2015 ከሴልቲክ ጋር የስኮትላንድን ፕሪሚየርሺፕን ካሸነፈ በሁዋላ የመጀመረያው ነው።

ፕሪሚየር ሊጉ 27 አመቱ ነው – ከኔዘርላንዳዊው እራሱ አንድ አመት ነው የሚያንሰው – እና በነዚህ ጊዜያት ፕሪሚየር ሊጉ ታላላቅ ተከላካዮችን አይቷል። ወደ አእምሮው የሚመጡት የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ሰዎች አራት ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው ቪሰነት ኮምፓኒ እና አምስት ጊዜ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊው እና የሻምፒዮና ሊግ አሸናፊው ጆን ቴሪ ናቸው፡፡
እንግሊዛዊውም ቴሪ በአንድ የፕሪሚየር ሊግ ሲዝን 15 ግቦች ብቻ የተቆጠረበት የአስደናቂው ቼልሲ ቡድን ውስጥ ዋነኛው አካል ነበር ፡፡ (ለማነፃፀር ባለፈው አመት በፕሪሚየር ሊጉ ታሪክ ጥሩ ሶስተኛ ተከላካይ የነበረው ሊቨርፑል 22 ግቦችን አስመዝግቧል)፡፡

ወደ ማንቸስተር የቀይ ጎን ስንመለከት እንደ ሪዮ ፌርዲናንድ ፣ ኒማያ ቪዲች ፣ ጃፓ ስታም ፣ ስቲቭ ብሩስ እና ጋሪ ፓሊስተር ያሉ ድንቅ ተከላካዮችን እናገኛለን።
ፌርዲናንት እና ቪዲክ በፈጠሩት ጥምረት በተከታታይ ሶስት አመታት የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊዎች ሆነዋል፡፡ ስታም እ.ኤ.አ. በ 1999 ሶስት ዋንጫዎችን ባሸነፈው ቡድን ውስጥ ማሽን የነበረ ሲሆን ብሩስ እና ፓሊስተር የ ሊጉ የመከላከል አጨዋወት የተገነባባቸው መሠረቶች ነበሩ ፡፡
ሲዝኑን ሙሉ ሳይሸነፍ ዋንጫ የወሰደው ቡድን አባል የነበረው ሶል ካምቤል እና የሁለት ጊዜ የሊጉ አሸናፊ እና የብዙዎቹ የምንግዜም ምርጡ ቶኒ አዳምስ የአርሰናል ሁለት ድንቅ ተከላካዮች ናቸው።

የቫን ዳይክን 2018/2019 ሲዝን ስንመለከት በእርግጥም በሮናልዶ እና በሜሲ ዘመን እንኳን የባልሎንዶር አሸናፊ መሆን የሚችል ተጫዋች ይመስላል።

ግን ከላይ የተጠቀሱት ተከላካዮች ሁሉ ቫን ዳይክ የሌለው አንድ ነገር አላቸው እሱም ሁለት፣ ወይም ከዛም በላይ የፕሪሚየር ሊግ አሸናፊ ሜዳልያ ነው። እርሱም የሊጉ አሸናፊ እስከሚኖረው ድረስ የሊጉ የምንግዜም ምርጡ ተከላካይነቱ ሊታሰብ አይችልም።
የፕሪሚየር ሊጉ ታላላቅ ተጨዋቾች ሁሉ አንድ ነገር ያረጋሉ ————- ፕሪሚየር ሊጉን ያሸንፋሉ ፡፡