የአውሮፓ ማህበረሰብ ዋንጫ ወይም ዩሮፓ ሊግ ረብዑ ግንቦት 21 ከምሽቱ 4 ሰአት ላይ ሁለቱን የለንደን ክለቦች አርሰናልና ቼልሲን በማፋለም ፍፃሜውን ያገኛል ፡፡
ቼልሲዎች ኤንትረ ፍራንክ ፈርትን አሸንፈው ነው ወደ ፍፃሜው ያመሩት አርሰናሎችም በበኩላቸው የስፔኑን ክለብ ቫሌንሺያን አልፈው ነው ዛሬ ባኩ ኦሎምፒክ ስታዲየም የደረሱት ፡፡ የማሪዚዮ ሳሪዎቹ ቼልሲዎች በኩል ሮበን ሎፍተስ ቼክ ከጉዳቱ እስካሁን አላገገመም የንጎሎ ካንቴ ጉዳት እና አንቶኒዮ ሩዲገር ደግሞ ለጨዋታው ሊሰለፉም ላይሰለፉም ይችላሉ ተብሏል ፡፡ በአርሰናል በኩል አሮን ራምሴ / ዳኒ ዌልቤክ / ሄክቶር ቤላሪን / ሮብ ሆልዲንግ እና ዴኒስ ሱዋሬዝ መሰለፋቸው አልተረጋገጠም ፡፡ ጨዋታውን ጣልያናዊው አልቢትር ጁአንሉካ ሮቺ የሚመራው ሲሆን በ2019 የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እርስ እርስ ግንኙነታቸው በመጀመሪያዋ ዙር በስታድ ፎር ብሪች ቼልሲ 3 ለ 1 መድፈኞቹን ሲያሸንፉ በሁለተኛዋ ዙር ጨዋታ ደግሞ በኤመሬተረስ ስታዲየም አርሰናሎች 2 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል ፡፡ ችልሲዎች የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግን 3ኛ ሆነው በማጠናቀቃቸው በቀጣይ አመት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መግባታቸውን አርጋግጠዋል ፡፡ ነገር ግን መድፈኞቹ አርሰናሎች ግን አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመግባት ግዲታ ቼልሲን ማሸነፍ ግድ ይላቸዋል ። በቼልሲ በኩል ኤደን ሀዛርድ ወደ ሪያል ማድሪድ ለማቅናት ከጫፍ በመድረሱ ይህ የዩሮፓ ሊግ ፍጻሜ የመጨረሻ የቼልሲ ጨዋታው አንደሚሆን ይጠበቃል ። በአርሰናሎች በኩል ወደ አሮጊቷ ጅቬንቱስ ማቅናቱ የተረጋገጠው አሮን ራምሴ በዚህ ጨዋታ የሚሰለፍ ከሆነ የመጨረሻው የአርሰናል ጨዋታ ይሆናል ።