ሊጠናቀቅ የአንድ ቀን እድሜ የቀረው የ2018/19 የኢንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ነገ  እሁድ ግንቦት 4 ቀን 2011 ዓም በ11 ሰአት ሁሉም ጨዋታዎች በተመሳሳይ ሰአት ይጠናቀቃሉ  ፡፡

 በአሜክስ ስታዲየም ከመውረድ ስጋት የተረፈው ብራይተን ሆቭ አልቢዮን ለሻምፒዮንነት የሚፎካከረውን ማንቸስተር ሲቲን ያስተናግዳል ፡፡ በመጀመሪያው ዙር በኢትሀድ እስታዲየም ማን ሲቲ በሰልጂዮ አጉዌሮ እና በራሂም ስተርኒግ ግብ ሁለት ለዜሮ ማሸነፉ ይታወሳል ሆኖም ማንቸስተር ሲቲዎች ይህ ጨዋታ ከምንም በላይ ነው ፡፡ የፔፕ ጋርዲዮላዎቹ ማን ሲቲዎች የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ይህንን ጨዋታ ማሸነፍ ግድ ይላቸዋል ሲቲዎች በአሜክስ እስታዲይም ላይ ድል ሚቀናቸው ከሆነ የሊቨርፑልን ውጤት ሳይተብቁ ዋንጫው ከፍ ማድረግ ይችላሉ ፡፡

በሌላ ጨዋታ በትሩፍ ሞር ስታዲየም 15 ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት በርንሌዎች 5ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙትን አርሰናሎችን ያስተናግዳሉ ፡፡ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በኤመሬትስ ስታዲየም መድፈኞቹ 3 ለ 1 ማሸነፋቸው ይታወሳል ፡፡ ሆኖም አርሰናሎች ምርጥ አራት ውስጥ ገብተው ማጠናቀቅ የሚችሉበት አጋጣሚ ቢጠብም አሰልጣኝ ዩናይ ኤመምሬ ለመሸነፍ አይጓዙም ምንም እንኳ አርሰናል የዩሮፓ ሊግን ማንሳት ከቻለ ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መግባት የሚችል ይሆናል ሆኖም አርሰናል ጋር በዩሮፓ ሊግ ለፍፃሜ የቀረበው ቼልሲ ቢሆንም አርሰናሎች ግን ለሻምፒዮንስ ሊግ ለምግባት ሲል ማሸነፍን ግዴታው አድርጎ ነው ወደ ሜዳ የሚገባው ግን የማሪዚዮ ሳሪ በቼልሲ ቤት ከመጡ ጀምሮ ምንም አይነት ዋንጫ ስላላሳኩ ዩሮፓ ሊጉን ለማንሳት አይግደረደሩም ስለዚህ ለመድፈኞ ትልቅ ፈተና ይሆንባቸዋል ፡፡

በሌላ ጨዋታ በኪንግ ፓወር ስታዲየም 9ኛ ደረጃ ላይ ያሉት ቀበሮዎቹ ሌስተር ሲቲዎች 3ኛ ደረጃ ላይ ያሉትን የምዕራብ ለንደኖቹ ቼልሲዎችን ያስተናግዳሉ ፡፡ በመጀመሪያው ዙር ጨዋታ በሰታም ፎረድ ብሪች እንግዳው ሌስተር ቼልሲን በሜዳወ 1 ለ 0 ማሸነፉ ይታወሳል ፡፡ ስለዘህ ሌስተሮች ለቼልሲ ትልቅ ፈተና ይሁኑባቸዋል ተብሎ ይገመታል ፡፡ ጨዋታው ለሁለቱም ክለቦች ብዙም ፋይዳ ባይኖረውም ከፍተኛ ፉክክር እንደሚታይበት ይገመታል ፡፡ የማሪዚዮሳሪዎቹ ቼልሲዎች ወደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ መግባታቸውን ቢያረጋግጡም ሶስተኛ ነታቸውን ለማስከበር ሌስተር ሲቲዎች ማሸነፍ ግድ ይላቸዋል ፡፡ በሪያል ማድሪድ እየተፈለገ ያለው የቼልሲው ኤደን ሀዛርድ ምናልባትም የበጨረሻው የፕሪሚየር  ሊግ ጨዋታው ሊሆን ይችላል ፡፡ እንዲሁም ቼልሲዎች በፊፋ የሁለት አመት የዝውውር እገዳ እገዳ ቢጣልባቸውም በይግባኝ እስካሁን እገዳው አልተጀመረባቸውም ሆኖም በዚህ የዝውውር መስኮት ብዙ ተጨዋቾችን ያስፈርማሉ ወይም በውሰት የሰጧቸው ተጫዋቾች ይመልሳሉ ተብሎ ይገመታል ፡፡ ይህንንም ተከትሎ የሌስተሩን ሀሪ ማጉ የርን ለማስፈረም ከሌሎቸች ክለቦች ጋር ፉክክራቸውን ጀምረዋል ፡፡ ስለዚህ ሀሪ ማጉየርም በሌስትር ማልያ የመጨረሻው የሊግ ጨዋታው ሊሆን ይችላል፡፡

በሌላ ጨዋታ ከአራት ቀን በፊት በሻምፒዮንስ ሊግ ትልቅ ታሪክ በተሰራበት በአንፊልድ ሮድ ስታዲየም የሊጉን ዋንጫ ለማንሳት ከማንቸስተር ሲቲ ጋር ለዋንጫ የሚፎካከረው ሊቨርፑል በሊጉ ምርጥ 6 ክለቦችን በቀላሉ እያሸነፈ የመጣውን በ7ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘውን ዎልቨር አምፕተንን ያስተናግዳል፡፡ በመጀመሪያው ዙር የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ሊቨርፑል በሞሊነክስ ስታዲየም ዎልቭስን 2 ለ 0 ማሸነፋቸው ይታወሳል ፡፡ ምንም እንኳ ለዎልቨስ ይህ ጨዋታ ጥቅም ባይኖረውም ለሊቨርፑሎች ይህንን ጨዋታ የሚያሸንፉ ከሆነ የማን ሲቲን ውጤት ጠብቀው ሲቲ የሚሸነፍ ከሆነ ሊቨርፑል ዋንጨውን የሚያነሳ ይሆናል ፡፡ የየርገን ክሎፕ ልጆች ከረጅም አመት የዋንጫ ድርቅ በኋላ ዋንጫውን የሚያነሱ ከሆነ በሊቨርፑል ቤት ታሪክ ፅፈው ያልፋሉ ፡፡  

በሌላ በጨዋታ በኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም የውጤት መቃወስ ውስጥ ያሉት ማንቸስተር ዩናይትዶች መውረዱን ካረጋገጠው ካርዲፍ ሲቲን ያስተናድዳሉ ፡፡ ከሻምፒዮንስ ሊግ ሙሉ ለሙሉ አለመግባታቸውን ያረጋገቱት ማን ዩናይትዶች የዛሬው ጨዋታ አብዛኞቹ የማንቸስተር ዩናይትድ ተጨዋቾች የመጨረሻ የሊግ ጨዋታቸው ሊሆን ይችላል ፡፡ ለአብነት ያክል ፖል ፖግባ ፣ዴቪድ ዴህያ ፣ አንደር ሄሬራ እና አሌክሲስ ሳንቼዛ የሚጠቀሱ ይሆናል ፡፡

በአዲሱ ቶተናህም ሆትስፐር ስታዲየም አራተኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ቶተናህሞች 8 ኛው ኤቨርተኖችን ያስተናግዳሉ ቶተናሞች ከምርጥ አራት ውስጥ የሚወጡት ተሸንፈው አርሰናል በርንሌይን 6 ለ 0 ማሸነፍ ግድ ይለዋል ስለዚህ  ቶተናሞች የሻምፒዮንስ ሊግ ፍፃሜው ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን የሚቀጥሉ ይሆናል ፡፡

በሌላ ጨዋታ ክሪስታል ፓላስ በርንማውዝን ፣ ፉልሃም ኒውካስትልን ፣ ሳውዝእምፕተን ሃድልስፊልድን ፣ ዋትፎርድ ዌስት ሀምን የሚያስተናግዱ ይሆናል ፡፡