የየርገን ክሎፑ ቡድን  መሀመድ ሳላህ ፣ ሮቤርቶ ፈርሚኒዮ ፣ ናቢ ኬታ አና አዳም ላላናን በጉዳት ምክኒያት ሳያሰልፍ ባርሴሎናን የገጠመው ሊቨርፑል ገና በ7ኛው ደቂቃ በቤልጄማዊው አጥቂ ኦሪጊ የመጀመሪያውን ጎል አስቆጥሮ ሊቨርፑልን ማነቃቃት ችሏል  ፡፡

 ከመጀመሪያው ግብ በኋላ ባርሴሎናዎች ተጭነው የተጫወቱ ቢሆንም በሊቨርፑል አንድ ለዜሮ መሪነት ወደመልበሻ ክፍል አምርተዋል የሊቨርፑሉ አንድሬ ሮበርትሰን ባጋጠመው ጎዳት  ከእረፍት መልስ  በጆርጂኒሆ ዋይናልደም ተቀይሮ ወጥቷል፡፡

 ከእረፍት መልስ  በ54ኛው ደቂቃ ከአሌክስአንደር አርኖልድ የተሸማውን ኳስ ጆርጂኒዮ ዋይናልደም በእግሩ በመምታት ኳስና መረብ አገኛኝቶ ባርሲሎናዎችን ይበልጡኑ ጫና ውስጥ ከተታቸው ፡፡

ከሁለት ደቂቃ በኋላ በ56ኛው ደቂቃ ዤርዳን ሻኪሪ ያሻማውን ኳስ ጆርጂኒዮ ዋይናልደም በግንባሩ በመግጨት ለሊቨርፑል 3ኛ ግብ አስቆጠረ ፡፡

የየርገን ክሎፖ ልጆች ታሪክ ለመስራት ቋምጠዋል ከክሎፕ በስተጀርባ የቀድሞ የሊቨርፑል ተጨዋች ስቴቨን ጄራርድ እና መሀመድ ሳላህ በተደበላለቀ ስሜት ይከታተላሉ በ79ኛው ደቂቃ የባርሴሎና ተጨዋቾችን መዘናጋት ተመልክቶ ከማዕዘን ምት አሌክስአንደር አርኖልድ ለአሪጊ ያቀበለውን ኳሽ በቀላሉ ወደግብ ቀየረው ፡፡

 አንፊልድ ተናወጠች መርሲሳይድ በቀይ ቀለም ደመቀች የሊቨርፑል ደጋፊዎች ጮቤ ረገጡ ሳልህ አላመነም ሜሲ ደንግጧል ይህ ሁሉ በአንፊልድ ላይ ታየ ጨዋታው መጠናቀቁን ቱርካዊው አልቢት ካኩር አበሰሩ የባርሴሎና ደጋፊዎች አንገታቸውን ደፉ ሊቨርፑል በተከታይ ለሁለተኛ ግዜ ለአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ፍጻም ደረሰ፡፡