ኢትዮጵያዊው አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ በሂቻም ኤል ጉሩዥ ተይዞ የነበረውን የወንዶች የዓለም የቤት ውስጥ የአንድ ማይል ውድድር በ1.44 በማሻሻል ቦስተን ላይ በኢትዮጵያውያን አቆጣጠር በ24/06/2011 ተጋጣሚዎቹን በድንቅ ብቃት በመቅደም 3፡47.01 በመግባት ለ21 ዓመታት ያልተደፈረውን ሪከርድ በማሻሻል አሸንፏል፡፡

በተመሳሳይ  ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ የካቲት 9/2011 ዓ. ም. በእንግሊዝ በርሚንግሐም በተካሄደ የቤት ውሰጥ የ1,500 ሜ. ሩጫ ውድድር  እኤአ በ1997 በ ሂቻም ኤል ጉሩዥ ተይዞ የነበረውን 3:31.18 ሪከርድ በ14 ማይክሮ ሰከንድ በማሻሻል 3:31.04 በመግባት ማሸነፉ ይታወሳል ።