ኢትዮጵያዊው አትሌት ሳሙኤል ተፈራ የካቲት 9/2011 ዓ. ም. በእንግሊዝ በርሚንግሐም በተካሄደ የቤት ውሰጥ የ1,500 ሜ. ሩጫ ውድድር  እኤአ በ1997 በ ኤል ጉሩዥ ተይዞ የነበረውን 3:31.18 ሪከርድ በ14 ማይክሮ ሰከንድ በማሻሻል 3:31.04 በመግባት አሸንፏል። አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻም ሳሚን ተከትሎበ 3:31.58 ሁለተኛ ሆኖ ጨርሷል።