36ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና እሁድ የካቲት 3 ቀን 2011 አ/ም በጃን ሜዳ በድምቀት ይከናወናል ።

በዚህ ውድድር ላይ በወጣቶች ከ1-6ኛ የወጡ በቀጥታ የሚመሩጡ ሲሆን በአዋቂዎች ደግሞ ከ1-5 ያሉት በቀጥታ ያልፉና 6ኛ ተመራጮች ደግሞ ባስመዘገቡት የተሻለ ሰዓት ተለይተው የሚካተቱ ይሆናል ።

በተጨማሪም በ43ኛው የአለም አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የሚሳተፉ ውጤታማ አትሌቶች የሚመርጡበት ትልቅ ውድድር ነው ።

36ኛው የጃንሜዳ ኢንተርናሽናል አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በኢቲቪ መዝኛና ቻናል ከማለዳው 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ድረስ ለ3 ሰዓታት ያህል የቀጥታ ስርጭት ሽፋን ያገኛል፡፡ በቀጥታ ስርጭቱ ላይ ታዋቂ አትሌቶች ውድድሮቹን እየተከታተሉ ትንተና ይሰጣሉ፡፡
በዚህ ውድድር ላይ ከ6 ያላነሱ አጋር የመንግስት መ/ቤት ኃላፊዎች፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፣ በርካታ ውጤታማ፣ ታዋቂና ስመ ጥር አትሌቶች፣የአትሌት ማናጀሮችና ተወካዮቻቸው፤ ከተለያዩ ተቋማት የሚገኙ ኃላፊ• ሁሉም የስፖርት ሚዲያ ተቋማት፣ የጎረቤት አገራት አትሌቶች እንዲገኙ ተጋብዘውበታል
ምንጭ ስለሺ ብሥራት – የኢአፌ ኮሙኒኬሽን ከፍተኛ ባለሙያ