የምሥራቅ አፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን ኮንግረስ ስብሰባ በአዲስ አበባ ጥር 4/2011 ዓ.ም ከማለዳው 3:30 ሰዓት ጀምሮ በካፒታል ሆቴል ተከናውኗል።

በስብሰባው መክፈቻ ለተሳታፊዎቹ ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ የኢአፌ ፕሬዝዳንትየእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፋለች።

የስብሰባው የክብር እንግዳ ክቡር አቶ ርስቱ ይርዳው የፌዴራል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር የመክፈቻ ንግግር አድርገዋል።

በተካሄደው  የአፍሪካ አትሌቲክስ ሪጅን የቦርድ አባላት ምርጫ ክብርት ኮሎኔል አትሌት ደራርቱ ቱሉ ም/ፕሬዝዳንት ሆና በሙሉ ድምፅ ተመርጣለች። ከዚህ ባለፈ ደራርቱ በአፍሪካ አትሌቲክስ ኮንፌዴሬሽን /CAA/ ውስጥ ሪጅኑን በመወከል የቦርድ አባል ሆና ተመርጣለች።

ሚ/ር ጂ ኢሥራም IAAFን በመወከል የምሥራቅ አፍሪካውን አትሌቲክስ ሪጅን IAAF ከአሁኑ በተሻለ ሊያግዘው እንደሚችል ቃል ገብተዋል ።

ምንጭ የኢአፌ