የፓትሪክ ሳንግ ከኪፕቾጌ ዉጤት ጀርባ ያለ ጀግና፡-
ፓትሪክ ሳንግ የቀድሞ የ3ሺ ሜትር መሰናክል ሩጫ አትሌት ነዉ፡፡ሳንግ በሩጫ ዘመኑ አገሩ ኬንያን በመወከል በታላላቅ ዉድድሮች 3 የብር ሜዳልያዎችን አስመዝግቧል፡፡እ.ኤ.ኣ በ1992ቱ የባርሴሎና ኦሎምፒክ አገሩን በ3ሺ ሜትር መሰናክል ሩጫ የብር ሜዳልያ ባለቤት ሲያደርግ፤በዓለም ሻምፒዮናም በ1991ዱ የቶክዮ/ጃፓን/ ሻምፒዮና እና በ1993ቱ የስቱትጋርት/ጀርመን/ ሻምፒዮናዎች ተመሳሳይ ክብሮችንነ ለሃገሩ አስገኝቷል፡፡
ከእንደ ኪፕቾጌ አይነት አትሌት ጋር መስራት አስደሳች መሆኑን የሚናገረዉ ሳንግ ከአትሌቱ ጋር ከአቀዱት በላይ ዉጤት ማስመዝገባቸዉን እና ይህ ደግሞ ከራሱ ዉጤት በላይ እንደሚያረካዉ ይገልጻል፡፡ወደ ዋናዉ ማራቶን በ2012 መግባቱን ያስታወሰዉ ሳንግ ከጅምሩ በ2013 ሃምቡርግ ማራቶንን 2:05:30 ለመግባት አቅደዉ የገቡ ቢሆንም በአጭር ጊዜ 2 ሰዓት ከ 03 እና 04 መሮጥ መቻሉን በማስታወስ የኪፕቾጌን የስኬት መንገድ ያስረዳል፡፡
በሩጫ ዘመኑ በራሱ የሚጠበቅበትን ያህል ዉጤት እንዳላስመዘገበ የሚያምነዉ ፓትሪክ ሳንግ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ ከሆነ በኋላ በተመዘገቡት ዉጤቶች ይበልጥ እንደሚረካ ለአይ.ኤኤ.ኤፍ ተናግሯል፡፡ኪፕቾጌ በ2018ቱ የበርሊን ማራቶን 2:01:39 በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰንን በእጁ ማስገባቱ ይታወሳል፡፡
ፓትሪክ ሳንግ እንደሚለዉ ከሆነ፣የኪፕቾጌ የስኬት ምስጢር የራሱ ጉብዝና መሆኑን በማንሳት ከአመጋገብ እስከ ፊዚዮ ቴራፒ የራሱን ጥንቃቄ ከማድረጉ ባሻገር ከአሰልጣኙ የሚሰጡትን የልምምድ ወቅት ስራዎች አንድም ሳይቀንስ ያጠናቅቃል ሲል መስክሮለታል፡፡ስፖርቱ የሚጠይቀዉን ህግ ሁሉ የሚፈጽም ፕሮፌሽናል አትሌት መሆኑ አሁን የደረሰበት ቦታ ላይ እንዲገኝ አግዞታል ሲልም ሳንግ ያክላል፡፡
ኢሉድ ኪፕቾጌ በ2016ቱ የሪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያዊዉን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ቀድሞ ያገኘዉን ጨምሮ በተለያዩ ዉድድሮች አንገቱ ላይ ካጠለቃቸዉ የወርቅ ሜዳልያዎች ዉስጥ ስምንቱ በማራቶን ስፖርት ያገኛቸዉ ናቸዉ፡፡ኬንያዊዉ አትሌት ባሳለፍነዉ የ2017/18 የዉድድር ዓመት በርካታ ድሎችን ያስመዘገበበት ዓመት ሲሆን በናይኪ ፕሮጀክት አማካይነት በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ማራቶንን ከ2 ሰዓታት በታች ለመሮጥ የተቃረበ አትሌት መባል የቻለበት ጊዜ እንደነበር የሚታወቅ ስሆን በዚህ እና መሰል ዉጤቶቹ የ2018 የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የ2017/18 ምርጡ አትሌት መባሉም የቅርብ ጊዜ ትዉስታ ነዉ፡፡የፓትሪክ ሳንግ ከኪፕቾጌ ዉጤት ጀርባ ያለ ጀግና፡-
ፓትሪክ ሳንግ የቀድሞ የ3ሺ ሜትር መሰናክል ሩጫ አትሌት ነዉ፡፡ሳንግ በሩጫ ዘመኑ አገሩ ኬንያን በመወከል በታላላቅ ዉድድሮች 3 የብር ሜዳልያዎችን አስመዝግቧል፡፡እ.ኤ.ኣ በ1992ቱ የባርሴሎና ኦሎምፒክ አገሩን በ3ሺ ሜትር መሰናክል ሩጫ የብር ሜዳልያ ባለቤት ሲያደርግ፤በዓለም ሻምፒዮናም በ1991ዱ የቶክዮ/ጃፓን/ ሻምፒዮና እና በ1993ቱ የስቱትጋርት/ጀርመን/ ሻምፒዮናዎች ተመሳሳይ ክብሮችንነ ለሃገሩ አስገኝቷል፡፡
ከእንደ ኪፕቾጌ አይነት አትሌት ጋር መስራት አስደሳች መሆኑን የሚናገረዉ ሳንግ ከአትሌቱ ጋር ከአቀዱት በላይ ዉጤት ማስመዝገባቸዉን እና ይህ ደግሞ ከራሱ ዉጤት በላይ እንደሚያረካዉ ይገልጻል፡፡ወደ ዋናዉ ማራቶን በ2012 መግባቱን ያስታወሰዉ ሳንግ ከጅምሩ በ2013 ሃምቡርግ ማራቶንን 2:05:30 ለመግባት አቅደዉ የገቡ ቢሆንም በአጭር ጊዜ 2 ሰዓት ከ 03 እና 04 መሮጥ መቻሉን በማስታወስ የኪፕቾጌን የስኬት መንገድ ያስረዳል፡፡
በሩጫ ዘመኑ በራሱ የሚጠበቅበትን ያህል ዉጤት እንዳላስመዘገበ የሚያምነዉ ፓትሪክ ሳንግ የኪፕቾጌ አሰልጣኝ ከሆነ በኋላ በተመዘገቡት ዉጤቶች ይበልጥ እንደሚረካ ለአይ.ኤኤ.ኤፍ ተናግሯል፡፡ኪፕቾጌ በ2018ቱ የበርሊን ማራቶን 2:01:39 በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰንን በእጁ ማስገባቱ ይታወሳል፡፡
ፓትሪክ ሳንግ እንደሚለዉ ከሆነ፣የኪፕቾጌ የስኬት ምስጢር የራሱ ጉብዝና መሆኑን በማንሳት ከአመጋገብ እስከ ፊዚዮ ቴራፒ የራሱን ጥንቃቄ ከማድረጉ ባሻገር ከአሰልጣኙ የሚሰጡትን የልምምድ ወቅት ስራዎች አንድም ሳይቀንስ ያጠናቅቃል ሲል መስክሮለታል፡፡ስፖርቱ የሚጠይቀዉን ህግ ሁሉ የሚፈጽም ፕሮፌሽናል አትሌት መሆኑ አሁን የደረሰበት ቦታ ላይ እንዲገኝ አግዞታል ሲልም ሳንግ ያክላል፡፡
ኢሉድ ኪፕቾጌ በ2016ቱ የሪዮ ኦሎምፒክ ኢትዮጵያዊዉን አትሌት ፈይሳ ሌሊሳን ቀድሞ ያገኘዉን ጨምሮ በተለያዩ ዉድድሮች አንገቱ ላይ ካጠለቃቸዉ የወርቅ ሜዳልያዎች ዉስጥ ስምንቱ በማራቶን ስፖርት ያገኛቸዉ ናቸዉ፡፡ኬንያዊዉ አትሌት ባሳለፍነዉ የ2017/18 የዉድድር ዓመት በርካታ ድሎችን ያስመዘገበበት ዓመት ሲሆን በናይኪ ፕሮጀክት አማካይነት በልዩ ሁኔታ ተዘጋጅቶ ማራቶንን ከ2 ሰዓታት በታች ለመሮጥ የተቃረበ አትሌት መባል የቻለበት ጊዜ እንደነበር የሚታወቅ ስሆን በዚህ እና መሰል ዉጤቶቹ የ2018 የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር የ2017/18 ምርጡ አትሌት መባሉም የቅርብ ጊዜ ትዉስታ ነዉ፡፡