የኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ፣ 8ኛ ሳምንት መርሃ ግብር ጨዋታዎች፣ ቅዳሜና እሁድ ተደርገዋል።

ቅዳሜ በአዲስ አበባ ስታድየም የተጫወቱት ኢትዮጵያ ቡናና ደደቢት ተጋጣሚዎቻቸዉን መርታት ችለዋል። የወልደያዎቹ አማረ በቀለና ብሩክ ቃልቦሬ በቀይ ካርድ በተወገዱበት ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና 2 ለ 0 ሲረታ፣ ጎል በማስቆጠሩ ረገድ ስኬታማ እየሆነ ያለዉ አቤል ያለዉና ጌታነህ ከበደ ባስቆጠሯቸዉ ጎሎች ደደቢትም ኢትዮ ኤሌክትሪክን በመርታት ሊጉን መምራቱን ቀጥሏል። ጎንደር ላይ፣ ፋሲል ከተማ ሃዋሳን ባስተናገደበት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ አቻ ዉጤት ጨዋታዉን ፈፅሟል።

እሁድ በተደረጉ የፕርሚየር ሊጉ ጨዋታዎች መከላከያና ሲዳማ ድል ሲያደርጉ ወደ መቀለ ያቀናዉ አዳማ 1 ለ 1፣ እንዲሁም ወደ አዲግራት ያቀናዉ ቅዱስ ጊዮርጊስ ያለ ጎል አቻ በሆነ ዉጤት አጠናቀዉ በ1 ነጥብ ተመልሰዋል።

እሁድ 15/04/2010 የተደረጉ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ 8ኛ ሳምንት ውጤቶች

መከላከያ 1 – 0 ድሬዳዋ ከተማ
13′ ምንይሉ ወንድሙ

ወልዋሎ 0 – 0 ቅዱስ ጊዮርጊስ

መቐለ ከተማ 1 – 1 አዳማ ከተማ
57′ አማኑኤል ገብረሚካኤል     63′ ዳዋ ሆቴሳ (ፍ.ቅ.ም)

ሲዳማ ቡና 3 – 1 ወላይታ ድቻ
9′ አብዱለጢፍ መሐመድ      74′ ዳግም

21′ ሐብታሙ ገዛኸኝ
66′ አዲስ ግደይ (ፍ.ቅ.ም)

ቅዳሜ 14/ 04/ 2010 ዓ/ም የተደረጉ ጨዋታዎች ውጤት

ኢትዮጵያ ቡና 2-0 ወልዲያ ከተማ
63′ (ፍ.ቅ .ም)፣ 81′ ኤልያስ ማሞ

ፋሲል ከተማ 2-2 ሀዋሳ ከተማ
73′ ያስር ሙጌርዋ       18′ አዲስአለም ተስፋዬ

85′ ዳዊት እስጢፋኖስ    90+4′ ታፈሰ ሰለሞን

ኤሌክትሪክ 1 – 3 ደደቢት
62′ አልሀሰን ካሉሻ    50′ አቤል ያለው፣ 52′፣ 85′ ጌታነህከበደ

ግርማይ መረሳ

ይሄን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ግርማይ መረሳ ነኝ።
ግርማይ መረሳ