መቀሌ ላይ ዛሬ በተከናወነ የኢትዮጵያ ዋንጫ አንደኛ ዙር ውድድር ፋሲል ከነማ ከሜዳው ውጪ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን 1-0 በማሸነፉ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።

ጨዋታው በፋሲል ከነማ 1-0 አሸናፊነት መጠናቀቁን ተከትሎ ዐፄዎቹ ወደ ሩብ ፍፃሜ መሸጋገር የቻሉ ሲሆን የአዳማ ከተማ እና ባህር ዳር ከተማ አሸናፊንም በቀጣይ የሚገጥሙ ይሆናል።