የ2019ኙን የአፍሪካ ዋንጫ እንድታዘጋጅ ተመርጣ ጉድ ጉድ ስትል የነበረችው ካሜሮን ውድድሩ ሊጀመር ትንሽ ሲቀረው በመሰረተ ልማት መጓደል ምክንያት በካፍ በመታገዷ ውድድሩን ለማዘጋጀት ግብጽ፣ ሴኔጋል እና ደቡብ አፍሪካ ውድድሩን በዋናነት የጠየቁ ሲሆን ደቡብ አፍሪካ የማስተናገድ ችግር የሌለባት ሀገር ብትሆንም በቅርቡ የአፍሪካ ዋንጫ እና የቻን አፍሪካ ዋንጫን በማስተናገዷ ውድቅ ተድርጎባታል ።

ሆናም ከሁሉም በላይ የማስተናገድ ፍላጎቷን በፊዲዮ እና በምስል አስደግፋ ከፍተኛ የማስተናገድ ፍላጎታን ለካፍ የገለፀችው የናይል ተፋሰስ ሀገሯ ግብፅ የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ  በሴኔጋል ዋና ከተማ ዳካር ባደረገው ስብሰባ የ2019ኙ የአፍሪካ ዋንጫ እንድታስተናግድ  በዛሬው እለት በአብላጫ ድምፅ ወስኗል።

ግብፅ በመሰረተ ልማትም ሆነ በአፍሪካ ዋንጫ ጥሩ ውጤት ቢኖራትም የአፍሪካ ዋንጫ መስራች ከሆኑት ሱዳን ፣ ኢትዮጵያ እና ደቡብ አፍሪካ ጋር መስራች መሆኗ ነው ጥሩ መነሳሳትን ፈጥሮላታል ።
ግብፅ 16 ድምፅ በማምጣት ነው ተፎካካሪዋን ሴኔጋልን አሸንፋ ለዚህ ክብር የበቃችው ። 24 ሀገራትን የሚያሳትፈው የ2019ኙ የግብፅ አፍሪካ ዋንጫ ግብፅ 8 ስታዲየሞችን አዘጋጅታለች ። የግብፁ አፍሪካ ዋንጫ በአምስት ከተማዎች ሲደረግ በዋና ከተማው ካይሮ ፣ በአሌክስ አንድሪያ ፣ በኢስማሊያ ፣ በፖርት ሰይድ እና በስዊዝ የሚካሄድ ይሆናል ።