ዛሬ በተደረገው የኢትዮጵያ ዋንጫ መከላከያ ድል ቀንቶታል ። በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ አብዛኛውን ዋንጫ በማንሳት ቀዳሚ የሆነው መከላከያ ከሁል ግዜ ተቀናቃኙ ቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር ባደረገው ጨዋታ መከላከያ ድል ቀንቶታል ።

ጨዋታው በተጀመረ 52′ኛው ደቂቃ ቴዎድሮስ ታፈሰ ብቸኛው የመከላከያን ግብ በፈረሰኞቹ መረብ አስቆጥሮ መከላከያን የምንግዜም ተቀናቃኙን ቅዱስ ጊዮርጊስን አሸንፏል።

ሁለቱ ክለቦች ባለፈው አመት በኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ፍፃሜ ላይ ተገናኝተው መከላከያ በመለያ ምት አሸንፎ ዋንጫውን ማንሳቱ ይታወሳል።
የያለፈው አመት ሻንፒዎናነቱን ለማሳካት መከላከያ ጉዞውን በድል ጀምሯል ።
ቅዱስ ጊዮርጊስም ወሳኝ ቁልፍና ወሳኝ ተጫዋቾቹ ከጉዳት ተመልሰው የአጥቂ መስመሩን ጠንካራ ቢሆንም የአጥቂዎቹ አለመግባባት እና በአጨራረስ ድክመት በረካታ ግቦችን አምክነው ተሸንፈዋል ።

የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ ዋንጫ ነገም ሲቀጥል ።

ረቡዕ ጥር 1 ቀን 2011 በ09:00 ሰአት ላይ ወልዋሎ ዓ.ዩ. ከ ፋሲል ከነማ ይጫወታሉ ።