ለአንድ ወር የዓለም እግርኳስ አፍቃሪን ቀልብ ስቦ የነበረው የ2018ቱ 21ኛው የሩሲያው ዓለም ዋንጫ ዛሬ ምሽት 12:00 ሰዓት ላይ ሞስኮ በሚገኘውና 81ሺህ ተመልካች በሚይዘው ሉዝንስኪ ስታዲየም ፈረንሳይ ከክሮሽያ በሚያደርጉት የዋንጫ ጨዋታ ፍጻሜዉን ያገኛል፡፡

ክሮሽያ ዛሬ ፈረንሳይን በሉዚኒኪ ስታዲየም የምትገጥመዉ የመጀመሪያ የአለም ዋንጫዋን ለማንሳት ፧ሲሆን ተጋጣሚዋ ፈረንሳይ ደግሞ በ6 የአለም ዋንጫ ተሳትፎዋ 3 ጊዜ ለፍጻሜ ድሳ አንድ ጊዜ ብቻ ያነሳችዉን ዋንጫ በድጋሚ ለማንሳት የምትፋለም ይሆናል ፡፡

አብዛኞቹ የስፖርት ተንታኞች የማሸነፍ እድሉን ለፈረንሳይ ቢሰጡም በወርቃማ ትውልዷ እየታገዘች ሳትታሰብ ለፍፃሜ የደረሰችው ክሮሽያ ዋንጫ ታነሳለች እያሉ የሚሞግቱም በርካቶች ናቸው፡፡

ይህን ጨዋታ 81ሺህ ተመልካች በስታዲየም፤ በመላው ዓለም ደግሞ 800 ሚሊየን ሰዎች በቴሌቪዥን መስኮት ይመለከቱታል ተብሎ ይገመታል፡፡

ፈረንሳይ በወርቃማዋ ትውልድ በኦልቬ ጅሩ በአጥቂ መስመር የክሮሺያን ተከላካዮችን ይፈትናል ተብሎ ይገመታል ።

የመሀል መስመሩን ደግሞ ፖል ፖግባ / ኑጎሎ ካንቴ / ኬሊዬን ምባፔ / በአንቶንዮ ግሪዝ ማን / እና ማቱዲ የመሀል መስመሩን አስፈሪ አድርገውታል ።

ፓቫርድ / ቫራን / ሳሙኤል ኡሚቲቲ / ሄርናዴዝ ደግሞ በተከላካይነት የኻላ ደጀን ናቸው ።
የግብ ሀላፊነቱን ደግሞ የቶተናሙ ሂጎሎ ሎሪየስ በበረኝነት ለዋንጫው ከ ፈረንሳይ ብሄራዊ ብድን ጋር የሚፋለሙ ይሆናል ።

ፈረንሳይን በአምበልነት በረኛው ሂጎሎ ሎሪየስ ይመራል ተብሎ ይገመታል ።
በአንጻሩ የክሮሺያ ብሄራዊ ቡድን ከጥሎ ማለፉ ጀምሮ በየጨዋታው መቶ ሀያ ደቂቃ ተጋድለው ነው ለፍጻሜው የቀረቡት
ክሮሺያዎችም በበኩላቸው ሱባሲች በበረኝነት የኋላ ግርማሞገስ ያመሻል ተብሎ ይገመታል ።

በተከላካይነት ዲያሌድ ሎቭረን / ቪዳ / ስትሪንች / ቭርሳሊኮ ዛሬ ምሽት ለዋንጫው ይጋደላሉ ተብሎ ይገመታል ።

በ ረቢች / ፐርሲች / ሉካ ሞድሪች / ብሮዞቢች / ራኪቲች በመሀል መስመር ዛሬ ደምቀው ያመሻሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
በአጥቂ መስመር ደግሞ ማንዙኪች ፈረንሳይን ይፈትናል ። ለክሮሺያን ሉካ ምድሪች በአምበልነት ያገለግላል ።