በኢምሬትስ ስቴድየም አርሰናል ከቸልሲ ያደረጉት ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ ዉጤት ተጠናቀቀ።

የመጀመርያዉ አጋማሽ ያለ ጎል የተጠቀቀ ሲሆን፣ በጥሩ የማጥቃት እንቅስቃሴ ላይ የነበሩት አርሰናሎች የመጀመርያዉን ጎል ማስቆጠር ችለዋል። ጃክ ዊልሼር 63ኛዉ ደቂቃ ላይ ግሩም ጎል አስቆጥሮ አርሰናልን መሪ ማድረግ ችሏል። ነገር ግን ከ4ት ደቂቃዎች በኋላ ኤዲን ሃዛርድ ላይ በተሠራ ጥፋት የተሰጠዉን ፍፁም ቅጣት ምት ራሱ ሃዛርድ አስቆጥሮ ቸልሲዎች አቻ ሆነዋል።

84ኛዉ ደቂቃ ላይ ማርኮስ አሎንሶ ከዛፓኮስታ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ጎልነት ቀይሮ ቸልሲዎችን ወደ መሪነት መዉሰድ ችሎ ነበር። ነገር ግን፣ መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ በተሰጠዉ 4 የጭማሪ ደቂቃ ማርኮስ አሎንሶ ከጎል ክልሉ በሚገባ ማራቅ ያልቻላትን ኳስ ተጠቅሞ ቤለሪን 92ኛዉ ደቂቃ ላይ በግሩም ሁኔታ የአቻነት ጎል በማስቆጠር አርሰናል በሜዳዉ ሳይሸነፍ እንዲወጣ አድርጎታል።

አልቫሮ ሞራታ ግልፅ ጎል የማግባት ዕድሎችን ሳይጠቀምባቸዉ ቀርቷል። የሁለቱም ክልብ ግብ ጠባቂዎችም ጎል መሆን የሚችሉ ኳሶችን በጥሩ ብቃት ማዳን ችለዋል።

ዉጤቱን ተከትሎ ቸልሲዎች በ46 ነጥብ ሦስተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ፣ አርሰናሎች በ39 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

ግርማይ መረሳ

ግርማይ መረሳ

ይሄን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ግርማይ መረሳ ነኝ።
ግርማይ መረሳ