በእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ የ11ኛዉ ሳምንት መርሃ ግብር ቅዳሜ ስድስት ጨዋታዎች ሲደረጉ፣ እሁድ ከሚደረጉት አራት ጨዋታዎች መካከል ሁለቱ ትልቅ ግምት የሚሰጣቸዉ ጨዋታዎች ናቸዉ።

በኢቲሃድ፣ ማንቸስተር ሲቲ አርሰናልን የሚያስተናግድበት ፣ እንዲሁም የማንቸስተር ከተማ ሌላዉ ክለብ ማንቸስተር ዩናይትድ ወደ ስታምፎርድ ብሪጅ የሚያቀናበት ጨዋታ በሳምንቱ ከሚደረጉት ጨዋታዎች መካከል በጉጉት የሚጠበቁ ናቸዉ።

ቅዳሜ፣ ሊቨርፑል ዌስትሃም ዩናይትድን የሚጎበኝ ሲሆን፣ ቶተንሃም ሆትስፐር በደረጃዉ ግርጌ ላይ የሚገኘዉን ክርስትያል ፓላስን ይገጥማል።

አጠቃላይ የሳምንቱ ጨዋታዎች

ቅዳሜ፣ 25/ 2010 ዓ/ም

ስቶክ ሲቲ ከ ሌይስተር ሲቲ        9፡30
ሃደርስፊልድ ከ ዌስትብሮም       12፡00
ኒዉካስትል ከ በርንማዉዝ         12፡00
ሳዉዛምፕተን ከ በርንሌይ          12፡00
ስዋንሲ ከ ብራይተን                  12፡00
ዌስትሃም ከ ሊቨርፑል               2፡30

እሁድ፣ 26/2010 ዓ/ም

ቶተንሃም ከ ክርስትያል ፓላስ      9፡00
ማንቸስተር ሲቲ ከ አርሰናል        11፡15
ቸልሲ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ    1፡30
ኤቨርተን ከ ዋትፎርድ                1፡30

 

ግርማይ መረሳ

ግርማይ መረሳ

ይሄን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ግርማይ መረሳ ነኝ።
ግርማይ መረሳ