አሜሪካ ከሩስያዉ የዓለም ዋንጫ ዉጭ ሆነች።

በሰሜን፣ መካከለኛዉና ካሪብያን ሃገራት ዞን (ኮንካ ካፍ) ሦስት ሃገራት በቀጥታ የዓለል ዋንጫ ተሳትፎን የሚያገኙ ሲሆን አራተኛ ደረጃን ይዞ የሚያጠናቅቀዉ ሃገር በፕሌይ ኦፍ የሚጫወት ይሆናል። አሜሪካ አምስተኛ ደረጃን ይዛ በማጠናቀቋ ከ2018ቱ የሩስያ ዓለም ዋንጫ ዉጭ መሆኗ ተረጋግጧል።

ከዚህ ዞን ሜክሲኮ፣ ኮስታሪካና ፓናማ በቀጥታ የዓለም ዋንጫዉን ተሳትፎ ያገኙ ሃገራት ሲሆኑ ሆንዱራንስ ከአዉስትራሊያ ጋር በፕለይ ኦፍ ትገናኛለች።

አስቀድማ ወደ ኣለም ዋንጫዉ ማለፏን ያረጋገጠችዉን ኮስታሪካን የገጠመችዉ ፓናማ 2 ለ 1 በማሸነፍ በቀጥታ ወደ ሩስያ የሚወስዳትን የሦስተኝነት ደረጃን ስትይዝ ሆንዱራስ በተመሳሳይ በቀዳሚነት ወደ ሩስያ የሚያደርሳትን ደረጃ ያረጋገጠችዉን ሜክሲኮን 3 ለ 2 በሆነ ዉጤት በመርታት ለፕለይ ኦፍ በቅታለች።

ወደ ትሪንዳድና ቶቤጎ አቅንታ የመጨረሻ ጨዋታዋን ያደረገችዉ አሜሪካ 2 ለ 1 ተሸንፋ ከዓለም ዋንጫዉ ዉጭ ሆናለች። ከፓናማና ሆንዱራስ የተሻለ የጎል ክፍያ ያላት አሜሪካ የ19 ዓመቱን የክርስትያን ፑሊሲችን የአቻነት ጎል እንደማነቃቂያ ሳትጠቀምበት ቀርታለች።

ካላት የጎል ክፍያ አንፃር አሜሪካ አቻ ዉጤት በቀጥታ ወደ ሩስያ ሊወስዳት ይችል ነበር።

የኮንካ ካፍ የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ደረጃ

ሃገር                ነጥብ       ጎል

1. ሜክሲኮ       21           9
2. ኮስታሪካ       16           6
3. ፓናማ           13           -1
4. ሆንዱራስ      13          -6
5. አሜሪካ         12           4
6. ትሪንዳድ        6            -12

ግርማይ መረሳ

ግርማይ መረሳ

ይሄን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ግርማይ መረሳ ነኝ።
ግርማይ መረሳ