የቀድሞዉ የሳዉዛምፕተን አሰልጣኝ ክላዉድ ፑዌል የሌይስተር ሲቲን የአሰልጣኝነት መንበር ተረክበዋል።

ፑዌል በሳዉዛምፕተን ቆይታቸዉ በሁሉም ዉድድሮች ላይ 19 አሸንፈዉ፣ በ18ቱ ተሸንፈዉና በ10 ደግሞ አቻ መዉጣት የቻሉ ሲሆን፣ ሳዉዛምፕተንን ለኢ.ኤፍ.ኤል ፍፃሜ ማብቃት የቻሉ አሰልጣኝ ናቸዉ።

ፈረንሳዊዉ የ56 ዓመት ፑዌል በሞናኮ፣ ሊል፣ ሊዮንና ኒስ የሠሩ ሲሆን ቀጣዩ የቀበሮዎቹ አሰልጣኝ ሆነዉ ተሹመዋል። ሌይስተሮች ሻምፒዮኑ ራኒየሪን የካቲት ላይ ካሰናበቱ በኋላ ፑዌል በ2017 የቀበሮዎቹ ሦስተኛ አሰልጣኝ ሆነዋል። ቀበሮዎቹ ከዘጠኝ የፕርሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ በመርታት በ14ኛ ደረጃ ላይ ነዉ የሚገኙት።

ከራኒየሪ ስንብት በኋላ በጊዚያዊ አሰልጣኝነት ላይ የነበሩት ግሬክ ሼክስፒር በዋና አሰልጣኝነተ ከተሾሙ ከአራት ወራት በኋላ መሰናበታቸዉን ተከትሎ ማይክል አፕሌቶን ቀበሮዎቹን በጊዚያዊ አሰልጣኝነት መርተዋል።

ግርማይ መረሳ

ግርማይ መረሳ

ይሄን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ግርማይ መረሳ ነኝ።
ግርማይ መረሳ