የእንግሊዝ ፕርሚየር ሊግ ቅዳሜ፣ እሁድና ሰኞ በሚደረጉ የአስረኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቀጥሎ ይዉላል።

ቅዳሜ፣ ሰባት ጨዋታዎች ሲደረጉ፣ ምሳ ሰዓት ላይ የሳምንቱ ታላቅ ጨዋታ በማንቸስተር ዩናይትድና በቶተንሃም ሆትስፐር መካከል ኦልድ ትራፎርድ ላይ ይደረጋል። በእኩል 20 ነጥብ ላይ ሆነዉ የሚገናኙት ሁለቱ ክለቦች ማንቸስተር ከሃደርስፊልድ ሽንፈት በኋላ፣ ቶተንሃም ደግሞ ሊቨርፑልን በሰፊ ዉጤት አሸንፎ የሚያደርጉት ጨዋታ ነዉ።

11፡00 ላይ አምስት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን፣ አርሰናልና ሊቨርፑል በሜዳቸዉ፣ ማንቸስተር ሲቲ ከሜዳዉ ዉጭ ይጫወታሉ። ምሽት 1፡30 ላይ ደግሞ ቸልሲ ወደ በርንማዉዝ ሜዳ ተጉዞ የ10ኛ ሳምንት ጨዋታዉን ያደርጋል።

እሁድ ሁለት ጨዋታዎች የሚደረጉ ሲሆን፣ በተከታታይ ሳምንት አሰልጣኞቻቸዉን ያሰናበቱት ሌይስተር ሲቲና ኤቨርተን ይገናኛሉ። የዚህ ሳምንት የመጨረሻ ጨዋታ ሰኞ ምሽት ይከናወናል።

ቅዳሜ፣ 28/ 2010 ዓ/ም

ማንቸስተር ዩናይትድ ከ ቶተንሃም      8፡30
አርሰናል ከ ስዋንሲ                         11፡00
ክርስትያል ፓላስ ከ ዌስትሃም          11፡00
ሊቨርፑል ከ ሃደርስፊልድ                11፡00
ዋትፎርድ ከ ስቶክ ሲቲ                   11፡00
ዌስትብሮም ከ ማንቸስተር ሲቲ       11፡00
በርንማዉዝ ከ ቸልሲ                      1፡30

እሁድ፣ 29/ 2010 ዓ/ም

ብራይተን ከ ሳዉዛምፕተን               9፡30
ሌይስተር ከ ኤቨርተን                      12፡00

ሰኞ፣ 30/ 2010 ዓ/ም

በርንሌይ ከ ኒዉካስትል                  4፡00

ግርማይ መረሳ

ግርማይ መረሳ

ይሄን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ግርማይ መረሳ ነኝ።
ግርማይ መረሳ