ክሬግ ሼክስፒር የሦስት ዓመት ዉል ከፈረሙ ከአራት ወራት በኋላ ከሌይስተር ሲቲ አሰልጣኝነታቸዉ ተሰናበቱ።

በፕርሚየር ሊጉ 18ኛ ደረጃ ላይ የሚገኙት ቀበሮዎቹ ያለፉትን ስድስት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም። በተመሳሳይ፣ ክላዉዲዮ ራኒየሪ ማንም ሳይገምታቸዉ የፕርሚየር ሊጉን ዋንጫ ካነሱ ከ9 ወራት በኋላ ሲሰናበቱ ስድስት ጨዋታዎችን ያለ ማሸነፍ ተጉዘዉ ነበር።

የ53 ዓመቱ ሼክስፒር ከራኒየሪ ስንብት በኋላ ሌይስተርን በጊዚያዊነት ተረክበዉ ቡድኑን ከመዉረድ ካተረፉት በኋላና 12ኛ ደርጃን ይዞ እንዲጨርስ ካስቻሉት በኋላ ሰኔ ላይ ቋሚ መሆን ችለዉ ነበር። በተጠቀቀዉ የዉድድር ዓመት 16 ጨዋታዎችን አከዉነዉ 8ቱን ማሸነፍ ችለዋል። በቻምፒዮንስ ሊጉም እስከ ሩብ ፍፃሜ እንዲጓዝ አስችለዉታል።

የሼክስፒር ምክትል ማይክል አፕሊተን ቦታዉን በጊዚያዊነት ይረከባል።

ሌይስተር ሲቲ የፕርሚየር ሊግ 8ኛ ጨዋታዉን ሰኞ ምሽት ከዌስት ብሮም ዊች አልቢዮን ጋር አከናዉኖ 1 ለ 1 ከተለያየ በኋላ አሰልጣኙ ተሰናብተዋል። የሼክስፒር ስንብት ዌስትብሮምን ከገጠሙ በኋላ የተሰናበቱ ስድስተኛዉ አሰልጣኝ ያደርጋቸዋል። ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ማንቸስተር ዩናይትድን ከመልቀቃቸዉ በፊት ዌስትብሮምን ገጥመዉ 5 ለ 5 የተለያዩበት ከተጨመረ ደግሞ ሰባት ይደርሳል።

* ሚክ ማካርቲ፣ በ2012፣ 5 ለ 1 ከተሸነፉ በኋላ ከዎልቭስ አሰልጣኝነታቸዉ ተሰናብተዋል።

* አንድሬ ቪያስ ቦአስ በ2012፣ 1 ለ 0 ከተረቱ በኋላ ከቸልሲ አሰልጣኝነታቸዉ የተሰናበቱ ሲሆን፣ እሳቸዉን ተክተዉ የመጡት ሮቤርቶ ዲማቲዮ ከስምንት ወራት በኋላ ከቸልሲ ቤት ሲሰናበቱ በፕርሚየር ሊጉ ለመጨረሻ ጊዜ ያደረጉት ጨዋታ በዌስትብሮም 2 ለ 1 የተረቱበትን ጨዋታ ነዉ። ( በቻምፒዮንስ ሊጉ ከጁቬንቱስ ጋር ያደረጉት ጨዋታ የቸልሲ ቤት የመጨረሻ ጨዋታቸዉ ነዉ።)

* ሮቤርቶ ማንቺኒ ግንቦት 2013 ከማንቸስተር ሲቲ ቤት ከመሰናበታቸዉ በፊት በዌስትብሮም 1 ለ 0 ተርትተዋል።

* ፓዉሎ ዲካኒዮ 3 ለ 0 ከተረታ በኋላ ከሰንደርላንድ ስራዉ መስከረም 2013 ተሰናብቷል።

* ክሪስ ሁቶን ሚያዝያ 2014 ከኖርዊች ሲቲ ከመሰናበቱ በፊት 1 ለ 0 ተረትቷል።

* ሰር አሌክስ ፈርጉሰን ግንቦት 2013 የማንቸስተር ስራቸዉን ያቆሙት ከዌስትብሮም ጋር 5 ለ 5 ተለያይተዉ ነዉ።

ማን ሊተካቸዉ ይችላል?

ከግሬክ ሼክስፒር ስንብት በኋላ ቦታቸዉን ማን ሊተካዉ እንደሚችል እያነጋገር ሲሆን ከወዲሁ የበርካታ ትልልቅ አሰልጣኞች ስም እየተነሳ ይገኛል። ካርሎ አንቾሎቲ፣ ሳም አላርዳይስ፣ ዴቪድ ሞዬስ፣ አላን ፓርዲዉ፣ ክሪስ ኮልማን፣ ሮቤርቶ ማንቺኒና አሁን በጊዚያዊነት ቡድኑን የሚረከበዉ ማይክል አፕሊተን ስማቸዉ ከሌይስተር ጋር ተያይዟል።

ሌይስተር ሲቲ በመጪዉ ቅዳሜ የፕርሚየር ሊግ ዘጠነኛ ጨዋታዉን ከስዋንሲ ሲቲ ጋር ያደርጋል።

ግርማይ መረሳ

ግርማይ መረሳ

ይሄን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ግርማይ መረሳ ነኝ።
ግርማይ መረሳ