የ2024 እና የ2028 እ.ኤ.አ የኦሎምፒክ አዘጋጅ ሃገራት ይፋ ሆኑ”

ያለፉትን  የኦሎምፒክ ውድድሮች ለማዘጋጀት ፉክክር ውስጥ የነበረችውና በስተመጨረሻ በቤጅንግ እና ሎንዶን የተነጠቀችው ፓሪስ ከ2020ው የቶኪዮ ኦሎምፒክ ቀጥላ በ2024 ለማዘጋጀት ፍቃዱ ከአለም አቀፉ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ስታገኝ በተመሳሳይ በ1984 አዘጋጅ የነበረችው ሎሳንጀለስም ከአርባ አራት አመታት በኋላ በ2028 እንድታዘጋጅ መሰየሟን መቀመጫውን ደቡብ አሜሪካ ፔሩ ከተማ ያደረገው ኮሚቴ  አሳውቋል።

“የማዘጋጀት እድሉ የተሰጣቸው ያለምንም ምርጫ እና ድምፅ መስጠት በከተሞች መልካም ፈቃድ ነው” ያሉት የአለም አቀፉ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዘዳንቱ ቶማስ ቤች አያይዘውም ከአምስቱ የእዘጋጅ ፈቃድ ከጠየቁ ከተሞች መካከል ሃምቡርግ፣ ሮም እና ቡዳፔስት ራሳቸውን ከፉክክሩ ማግለላቸውን ተከትሎ እንደሆነ ተናግረዋል።
/
ምንጭ ቢቢሲ ስፖርት

ሞገሴ ሽፈራው

ይሄን ፅሁፍ ያቀረብኩላችሁ ሞገሴ ሽፈራው ነኝ። ከፎቶው ጎን ያለውን የፌስቡክ ምልክት ተጭነው ሊያገኙኝ ይችላሉ።