የአዲስ አመት አቀባበል በማስመልከት የወጣቶች ስፖርት ሚኒስተር ከኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና ሌሎች የስፖርት ማህበራት ጋር በመተባበር የስፖርት ውድድር መድረክ እንደሚያዘጋጅ ገለፀ፡፡

በሚኒስትሩ መስርያ ቤት ላይ በተካሄደው ጋዜጣዊ መግለጫ የሚኒስተሩ ሀላፊ አቶ ርስቱ ፣ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት ሻለቃ አትሌት ሀይሌ ገብረ ስላሴ ፣ የኦሎምፒክ ፕረዚደንት ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስ እንዲሁም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አቶ ጁነዲን በሻህ ተገኝተዋል፡፡

በአዲሱ አመት ሁሉም የስፖርት ፌዴሬሽኖች በስፖርት ልማት ትልቅ ለውጥ ለማምጣት ያቀዱ ሲሆን ህብረተሰቡ በስፖርት ልማት ውስጥ ተሳትፎ እንዲያደርግ እና ወጣቶች ከስፖርቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በጋራ ቃል የምንገባበት ጊዜ ነው ሲል ሚኒስተሩ ገልጿል፡፡

በዚህም ጷጉሜ 4 በአዲስ አበባ ስታድየም 8:00 ሰአት ላይ የተለያዩ ስፖርታዊ ውድድሮችን የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ቀኑን እንደ በአል ሳይሆን እንደ ስፖርት ነው  የምናየው ያለ ሲሆን የአገራቸው ስም ዐተለያዩ መድረኮች ያስተዋወቁ አትሌቶች የሚሳተፍበት 1500 ሜ ውድድር በወንዶች እና በሴቶች አዘጋጅቷል፡፡

በዚህ ውድድር በወንዶች በኩል

አትሌት   አሰፋ መዝገቡ

”         አበበ መኮንን

”         ሀይሌ ገብረ ስላሴ

”         ገዛሀኝ አበራ

”        ገ/እግዚአብሔር  ገ/ማርያም

”         ቀነኒሳ በቀለ   እና ሌሎች ሲሆኑ

በሴቶች በኩል

አትሌት ደራርቱ ቱሉ

”       ጌጤ ዋሜ

”       ፋጡማ ሮባ

”       ብርሀኔ አደሬ

”       ወርቅነሽ ኪዳነ   ወዘተ …የሚሳተፉ ይሆናል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በበኩሉ ቀጣዩ አመት ከስፖርታዊ ጨዋነት በተያያዘ የተሻለ ዓመት እንዲሆን ብዙ ማሻሻያዎች እየሰራሁነው ያለ ሲሆን በተጨማሪም ከ5 ያላነሱ አዳዲስ መመርያዎች አዘጋጅቻለሁ ብሏል፡፡

ጷጉሜ አራት  በእግር ኳስ ቅዱስ ጊዮርግስ ከ ኢትዮጵያ ቡና ( ሸገር ደርቢ ) ጨዋታቸው የሚያደርጉ ሲሆን  የሁለቱም ክለብ ተወካዮች ደጋፊዎቻቸው ተገኝተው የተለመደ ድጋፍ እንዲያደርጉላቸው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ቅዳሜ ጷጉሜ አራት ከሚከናወኑ ውድድሮች ቦክስ ፣ ገመድ ጉተታ ፣ ሰርከስ ፣ እግር ኳስ ፣ ሩጫ እና እንቁላል በማንኪያ የሚ ቀሱ ናቸው፡፡