የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከታዋቂው አለም አቀፍ የጃፓን ኒፖን ስፖርት ሣይንስ ዩኒቨርሲቲ ጋር በአጠቃላይ በስፖርት ሣይንስ ዘርፎች የተፈራረመ ሲሆን በተለይ ደግሞ፡-

1. በብቃት ምዘናና ትንተና፣ /Performance evaluation & analysis/

2. በስፖርት ህክምና፣ /Sport Medicine/

3. በስፖርት ስነ ምግብ፣ /Sport Neutrition/

4. በአትሌቲክስ ስፖርት ስልጠና፣ /Athletics Sport training/

5. በሴት አትሌቶች ጉዳይ፣ /Females in athletics Sport/ እና

6. በስፖርት ስነልቦና፣ /Sport Psychology/ ዙሪያ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የስምምነት ሰነድ / Memorandum Of Understanding – MOU / የጃፓኑን ዩኒቨርሲቲ በመወከል ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር ሂዴኪ ታካይ እና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽንን በመወከል ፕሬዝዳንቱ ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገ/ስላሴ የትብብር ስምምነት ፊርማቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በኒፖን ስፖርት ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ሰልጥነው ከወጡ ስፖርተኞች መካከልም በልዩ ልዩ የኦሎምፒክ ስፖርቶች ላይ በመሳተፍ 38 ወርቅ፣ 43 ብር፣ 47 ነሃስ በድምሩ 128 ሜዳልያዎች ማግኘት የቻሉትን አትሌቶችና ስፖርተኞች ያፈራ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲ መሆኑ ታውቋል፡፡

መረጃው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ነው