ብራዚላዊዉ የባርሴሎና ኮከብ ኔይማር ዳ ሲሊቫ ጁንየር የአለምን የተጫዋቾች የዝውውር ክብረወሰንን በመስበር የፈረንሳዩን ሀብታም ክለብ ፒኤስጂን ተቀላቅሏል፡፡ የ25 አመቱ ተጫዋች በ2013 ከብራዚሉ ሳንቶስ ወደ ስፔኑ ባርሴሎና አወዛጋቢ በሆነ 57 ሚ.ፓ የዝውውር ሂሳብ የተቀላቀለ ሲሆን ላለፉት አራት አመታትም በኑ ካምፕ አሳልፏል፡፡ በእኚህ አራት አመታትም ከሌላኞቹ የቡድን አጋሮቹ ሊዮኔል መሲና ሊዉስ ስዋሬዝ ጋር ለባርሴሎና ስኬት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት ችሏል፡፡ በ2011 ባርሴሎናን ከመቀላቀሉ አስቀድሞ የፊፋ ፑሽካሽ አዋርድን ዋይኒ ሮኒንና ሊዮኔል መሲን በመብለጥ አሸናፊ ሁኗል፡፡ አሁን ደግሞ ጉዞዉን ወደ ፓሪስ በማድረግ በ198 ሚ.ፓ ፒኤስጂን ተቀላቅሏል፡፡

የቱርኩ ሻምፒዮን ቤዚክታሽ የሊድስ ዩናይትዱን አጥቂ ክሪስ ዉድን ማስፈረሙን ይፋ አድርጓል፡፡ ተጫዋቹን ለማዛወር የፕርሚየር ሊጉ ክለቦች ስዋንሲ ሲቲ፣ ስቶክ ሲቲና ሳዉዝአፕተን ከፍተኛ ፍላጎት ቢያሳዩም በ20 ሚ.ፓ የዝውውር ሂሳብ የቤዚክታሽ ንብረት ሁኗል፡፡

የ18 አመቱ የሞናኮ አጥቂ ኪሊያን ምባፔ በባርሴሎና፣ ሪያልማድሪድ፣ ማንችስተር ሲቲና ፒኤስጂ በጥብቅ መፈለጉን ተከትሎ ከፈረንሳዩ ክለብ የመዉጣት ፍላጎቱ ጨምሯል፡፡

 የማንችስተር ዩናይትዱ አሰልጣኝ ጆዜ ሞሪንሆ የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ አስቀድሞ ሶስት ተጫዋቾችን ማስፈረም ይፈልጋሉ፡፡ በመጪው የዉድድር አመት ዩናይትድን ጠንካራ ተፎካካሪ ለማድረግ ከወዲሁ ቪክተር ሌንድሎፍንና ሮሜሮ ሉካኩን ወደ ቲያትር ኦፍ ድሪምስ የቀላቀሏቸዉ ሲሆን በቀጣይ ደግሞ የኢንተርሚላኑን ኳስ አቀጣጣይ ኢቫን ፐርሲችን ዝዉዉር ለመጨረስ እየተጉ ይገኛሉ፡፡ ነገር ግን ኢንተሮች ተጫዋቹን አሳልፈዉ ለመስጠት የፈለጉ አይመስሉም፡፡     ናይጄሪያዊዉ የማንችስተር ሲቲ አጥቂ ከለቺ ኢሄናቾ የህክምና ምርመራዉን በስኬት በማጠናቀቅ ወደ ሌሲስተር ሲቲ ተቀላቀለ፡፡ ወጣቱ ባለተሰጥኦ በቀበሮዎቹ ቤት አዲስ ብስራት ለሚመኙት ደጋፊዎች መልካም ዜና ሁኖላቸዋል፡፡

 ኔይማርን በፒኤስጂ የተነጠቁት ባርሴሎናዎች የእሱን ተተኪ ለማግኘነት ፊታቸዉን ወደ ፕርሚየር ሊጉ በማዞር በሁለት ተጫዋቾች ላይ ኢላማቸውን አነጣጥረዋል፡፡ በቀድሞ ተጫዋቻቸዉ ከክለባቸዉ መልቀቅ የተበሳጩት በርካታ የባርሴሎና ደጋፊዎች የኔይማርን ማልያ በአደባባይ ያጋሃዩት ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎችም ትችታቸውን እየሰነዘሩ ይገኛሉ፡፡ በኔይማር ዝዉዉር 198 ሚ.ፓ ወደ ካዝናቸዉ የከተቱት ባርሳዎችም የሊቨርፑሉን ፊልፕ ኮቲንሆንና የቼልሲዉን ኤደን ሃዛርደን ወደ ኑ ካምፕ ለማስኮብለል ከወዲሁ ፍላጎት አሳድረዋል፡፡

 የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርሰን ቪንገር ስለቺሊያዊዉ የክለባቸዉ ኮከብ ያላቸውን እምነት እንዲህ ሲሉ ገልፀዋል:- ሳንቼዝ የክለባችን ዉሳኔ ያከብራል እስከ ዉድድር አመቱ መገባደጃም በኤምሬትስ እንደሚቆይ ተስፋ አድርገዋል፡፡