የ2017 የዳይመንድ ሊግ ዉድድር በርካታ ከተሞችን እያቆራረጠ የሲዉዘርላንዷን ዙሪክ ከተማ ትናንት ምሽት መዳረሻዉ አድርጓል፡፡
መለዉ አለምን ቁጭ ብድግ እያደረገና የአትሌቶችን እህል
አስጨራሽ ትግል በግልፅ ያሳየዉ የ5ሺ ሜትር የወንዶች ዉድድር ከለንደኑ የአለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ማግስት እንግሊዛዊዉን ሞህፋራህና ኢትዮጵያዉያን አትሌቶችን በድጋሚ አገናኝቶ አምሽቷል፡፡
እስከመጨረሻው ሰዓት አንገት ባንገት ትንቅንቅ በነበረበት ምሽት የሞፋራህ የአጨራረስ ብቃት የአሜሪካዊዉ ፓዉል ቺሊሞ ሙክታር እንድሪስን መጥለፍ መቻልና የኢትዮጵያን የመጨረሻ ሰዓት የአጨራረስ ቴክኒካቸውን መቀየር አለመቻላቸው ተከትሎ የ34 አመቱ ሞሃመድ ፋራህ በ13:06.05 በሆነ ጊዜ ዉስጥ ዉድድሩን በበላይነት አጠናቋል፡፡
የአሜሪካዉ ፓዉል ቺሌሞ የሙክታርነ አንገት በመጎቱ እና
ሙክታር እና ዮሚፍ እርስ በርስ ተጠላልፈው የመጨረሻውን መስመር እንደዋና በደረታቸው ተዘርረው እዲገቡ በማድረግ ለሞፋራህ ማሸነፍ አስተዋጽኦ ከማበርከቱ በተጨማሪ ሀለተኛ የወጣ ቢሆንም ዉጤቱ በሰራው ጥፋት ምክኒያት ተሰርዟል ፡፡
ኢትዮጵያዉያኖቹ ሙክታር እንድሪስ ዮሚፍ ቀጀልቻና ሰሎሞን ባረጋ ከ2-4 ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል፡፡
ሌላኞቹ ኢትዮጵያዉያን የኔዉ አላምረዉና ብርሃኑ ለገሰ 6ኛና 9ኛ
ወጥተዋል፡፡