የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሀይሌ ገብረሥላሴ ….

ለዚህም ነው ሞፋራህ 600 ሜትር እና ሁለት ዙር  ሲቀር የሚሄደው፡፡ እሱ የተለየ አትሌት አይደለም፡፡የተለየው ከጀርባው ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ለኛ ከባዶች የነበሩት ያ ቴክኖሎጂ ልጁ ሁለት ዙር አካባቢ ሲቀር እግሩን ብቻ ነው የሚልከው በቃ set up ተደርጓል፡፡                   

             እርምጃን በተመለከተ ሁለት አትሌቶች አያልነሽ ደጀኔ እና አስካለ ድንቄሳ ለንደን ላይ ቀርተዋል፡፡ ያው የቀሩበት ምክንያት እንደሚታወቀው ይሄንን እድል አናገኝም በማለት እዚህ ለንደን መጥተን ከሚል አንጻር እንጂ  ሌላ ምንም እንትን እንደሌለ እኔ ምንም አልጠራጠርም፡፡     

            

         ምክትል ፕሬዝዳንት ገብረእግዚአብሔር ገብረማሪያም ………በጣም ቢቀዘቅዝ እንኳን እናንተ ሞ ፋራህን ስለማትችሉት በፊኒሽግ ከሰድስት እስከ አምስት ዙር ሲቀር ወጥታችሁ የቻላችሁትን ያክል ሞክሩ ብለናል፡፡…..      

         ክቡር አቶ ዱቤ ጂሎ   …..በመጀመሪያ ደረጃ አሰልጣኞቻችን ሞ ፋራህ ምንድነው የሚያደርገው? የሞ ፋራህ የአሯሯጥ ስልት ምንድን ነው ይለዋወጣል፡፡  በየዓመቱ ይለዋወጣል፡፡ ለምሣሌ ቤጀንግ ላይ የነበረው ሩጫ ለንደን ላይ አልድገመውም፡፡  

       የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ እና የፌዴሬሽኑ ኃላፊዎች በለንደን አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዙሪያ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ነሃሴ 13 ቀን 2009 ዓ.ም ዝግጅታችን የመግለጫውን ጭብጥ የዜና ዘገባ ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በመግለጫው ላይ የተነሱ ጥያቄዎችንና መልሶችን ደግሞ እንደወረዱ ከዚህ በታች አቅርነዋል፡፡        

          ጥያቄ፡- የመጀመሪው ጥያቄዬ ለአትሌት ገብረእግዚአብሄር ነው፡፡ አትሌት በነበርክበት ሰአት የኢትዮጵያን  ቡድን ታውቀዋለህ፡፡ አሁን ደግሞ የቡድን መሪ ሆነህ ነበር የሄድከው እና ከውጤቱም አንፃር እንዲሁም ደግሞ ከነበረው ዝግጅት አንጻር ለዚህ ስራ አስፈፃሚ የቤት ስራ ይሆናል ብለህ ያመጣኸው ነገር ምንድን ነው ? ይህንን ማስተካከል  አለብን ክፍተት ነበር ብለህ ያሰብከውን ብታስረዳን ?  ምክንያቱም ከዚህ የቡድን ስሜት ለመፈጠር የተሰራው ስራ ላይ የተወሰኑ ክፍተቶች  እንዳላባችሁ የገባኝ ነገር አለ፡፡  ሌላው ለዚህ ከሩጫ ተወዳዳሪዎች በተያያዘ  አትሌቶች የቀሩ አሉ የሚባል ነገር አለና እውነት የቀሩ አትሌቶች አሉ እነማን ናቸው ?        ጥያቄ፡-  በእግር ኳስ ያለውን ችግር ከኋላ አሠልጣኙ ካልተቆጠጠረ ቡድኑ ውጤት ሊያስመዘግብ  አይችለም፡፡ በአትሌቲክሱም እንደዛው ነው፡፡ አመራሩ ላይ ያላችሁ ሰዎች በዘርፉ ላይ ያላፋችሁ እንደመሆኑ መጠን  ፌዴሬሹን ነባር እና አዳዲስ አትሌቶችን አንድ ላይ አሰባጥሮ ጥሩ ስሜት ይጎድላል፡፡ የሚጠበቀውን ያህል ተሠርቷል ብዬ አላምንም ወደፊትስ ምን ለመስራት አቅደችኋል? ሲኒየሩ አትሌት በመኪና እየመጣ ትሬኒንግ የሚያደርግ ከሆነ ፍሬሹ ጋር እንዴት ነው ተግባብቶና ተመጣጥኖ በአንድ ላይ ተገናኝቶ ሊስራ የሚችለው? ሞፋራህ ከእንግዲህ የትራክ ውድድር ላይ አይገኝም ከሌሎች የአሜሪካ እና የኬኒያን ከመሳሰሉ ጠንካራ አትሌቶች ጋር ጥሩ ተፎካካሪ ሆኖ ለማሸነፍ የሚሰሩ ስራዎች ካሉ በሱ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥበት?  

    ጥያቄ፡- ይህ ጥያቄ ቀጥታ የሚመለከተው ሀይሌ ገብረስላሴን ነው፡፡ የልምምደ ጫና መቋቋም አንዱ ችግር እንደሆነ ገልፀሃልና አትሌቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ በግላቸው ነው የሚሠሩት የብሄራዊ ቡድን ውድድር ሲመጣ ነው ከብሄራዊ ቡድን አሠልጣኞች ጋር የሚሠሩት እና በግላቸው ከሚሠሩት  የተሻለ ጫና ያለው ትሪኒንግ አትሌቶች እንዲያርጉ ለማድረግ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኑ ምን ስልጣን አለው? ምን ሀላፊነትስ አለው?     

    ጥያቄ፡- የዛሬ ዓመት ከሪዮ ኦሎሚፒክ በፊት ከውድድሩም ሆነ በኋላ ፌዴሬሽኑን የመምራት እድሉን ካገኘን ነገሮች በተለየ እና በተሻለ መንገድ እናስኬዳለን ብላችኋል ነበር፡፡ ወደ ስልጣን ከመጣችሁ ወደ ስምንት ወራት ሆኗልና በፊት ከነበረው በተለየ መንገድ አደረግን የምትሉት ነገር ምን አለ?     

    ጥያቄ፡- ሌላው ጥያቄ ለክቡር አቶ ዱቤ ጂሎ ነው፡፡ ሞ ፋራህ በአስር ሺ ሜትር ላይ እንዴት ነበር የሮጠው የሚል አይተን አምስት ሺ ሜትር ተዘጋጅተናል ብላችኋል፡፡ ሞ ፋራህ አዲስ አትሌት አይደለም  ከዴጉ ጀምሮ አምስት ሺ ሜትር በለንደን ከተሸነፈበት ውጪ ተሸንፎ አያውቅም፡፡ አሯሯጡ ብዙ የተለየ ነገር ያለው አይመስለኝም፡፡ ከውድድሩ በፊት በአስር ሺ ሜትር ውድድር ላይ እንደ አምስት ሺው በተለየ ሁኔታ መዘጋጀት ለምን አልተቻለም የሚል ጥያቄ አለኝ?    

   ጥያቄ፡- ሀይሌ ሞ ፋራህ ቴክኖሌጂ ነው ብለሃል፡፡ ይህ ማለት በቴክኖሎጂ የታገዙ ነገሮች  የኦራገን ናይክ ስፖንሰር ውስጥ የተለያዩ ነገሮች ይኖራሉና እኔ በግሌ ይህንን ማወቅ ስለምፈልግ ብትነግረኝ፡፡ ይህን ወደ እኛ ጋር በማምጣትስ ለምን አንጠቀመውም?  

     (ከታች ያለውን መልስ የሰጠው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሀይሌ ገብረሥላሴ ነው፡፡)      

         መልስ፡- የመቆጣጠር እና የማመጣጠን ነገር ይቀራል ለተባለው አዎ በጣም ይቀራል፡፡ ሲኒየር እና ወጣት ማቀናጃት የሚለው ነገር አንዱ ፈተና ውስጥ የከተተን እሱ ነው፡፡ አንደኛው የትነው የምትሄደው ስላልነው ያኮርፉል፡፡ ለ7 እና 8 ዓመት የለመደው ሌላ ሲስተም ነው በቃ ተመለስ ስንል  እንዴት ተነክቼ ይላል፡፡ ደግሞ ይሳብና በጣም ወደማንፈልገው ደረጃ ይደርሳል፡፡ ለእናንተ ምን እንነግራችኋላን የምታውቁት ነገር ነው፡፡ አንደንድ ነገሮች እንደውም ዱብዳ ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች እያስታመምን እያባበልን መሆን ያለበት ወጣቶች እማ የሚወጡት ሲኒየሮቹ ጋር ሲቀናጁ ነው፡፡ እኔ አስታውሰላሁ ቀነኒሳ በቀለ ወደኛ ሲመጣ ስፒድ ነበረው፡፡ ኢንዱራንስ የሚባል ነገር ግን አልነበረውም፡፡ ከኛ ጋር ትሬኒግ በጣም በድግግሞሽ ይሰራ ነበር፡፡ እኔ ለስለሺ እለው ነበር፡፡ ስለሺ የለም እንጂ ምስክር ይሆንኝ ነበር፡፡ ይሄ ልጅ በጣም ፍጥነት አለው ኢንዱራንስ ከቻለ ጥሎን ይሄዳል ማንም አያቆመውም እለው ነበር፡፡ እንዳልኩት ዓመትም አልፈጀበትም ጥሎን ሄደ፡፡ ይሄ ልጅ እኛ ባንኖርለት ደግሞ ስፒዱን ብቻ  ይዞ ይቀር ነበር፡፡   

         ስለዚህ አሁንም እነዚህን የማቀናጀት ነገር ግድ ይላል፡፡  ዘንድሮ ብዙ ነገሮችን አልፈን የመጣነው ልጆቹ  የማኩረፍ ነገር ይኖራል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ደግሞ ወደ ማትፈልጉት ነገር ይሄዳሉ፡፡ እኛ ለመቅጣት ምንም ችግር የለብንም ማንንም ለመቅጣት አንፈልግም፡፡ እኛጋ ስራ አስፈፃሚውም፣ ቴክኒኩም በሉት እንደ አስተዳደሩም በመቅጣት ብቻ አያምኑም፡፡ መቅጣት ምንም አያደርግም፡፡ በመጀመሪያ መማር ማስተማር  ነው መቅደም ያለበት፡፡  ለመቅጣት ቅጣት ከሆነ ቅጣት ነው ሮናንልዶ 5 ጨዋታ ተቀጣ ሲባል ይሄ ትልቅ  ግዙፍ የሆነ ነው አይደል? ግን ሮናልዶ ብዙ ህጐችን ያውቃል ያቺን ሲተላለፍ ተቀጣ፡፡ እኛ ግን መጀመሪያ እስኪ እናሳውቃቸው የሚለውን ነው እና ወዳፊት ከነሱ ጋር ሲኒየር አትሌቶች ጋር የምንሰራው ምንድነው? የሚለውን ነገር በጣም ብዙ ስራዎች ይኖሩናል፡፡

       ከተጠየቁት ጥያቄዎች  ሌላው ወዳዚህ ስትመጡ ምን ለማድረግ አስባችሁ ነበር? ምን ለመቀየር አሰባችሁ? ለሚለው አሁን እንግዲህ ይሄንን አድርገናል ብንላችሁ በጣም ከባድ ነው፡፡ እኔ መጀመሪያ ቁጥር አንዱ የነበረ ነገር ልንገረችሁና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በጣም አጣብቂኝ ውስጥ የነበረበት ሁኔታ ነው፡፡ እኛ የመጣነው በዶፒንግ ኬዝ አሁን እንደዚህ ከለፈ በኋላ ሁላችንም ሲንፒል አድርገን እናየዋለን፡፡ እዚህ የተቀመጥነው ምናልባትም ለንደንም ላይ ላንገኝ እንችል ይሆናል፡፡ አንዱ ከሠራነው እሱ ነው፡፡ ሁለተኛ ነገር ልናመጣው የቻልነው ነገር አንዱ የቡድን ስራ ነው፡፡ ማለት እኛ ቡድን ስራ ማለት ደግሞ አንዱ አንዱን አድክም ተብሎ ብቻ አይደለም፡፡ የጋራ የሆነ በኛ ግዜ የነበረ በጋራ ሲሆን  ሲኒየሩ ከወጣቱ ጋር ሲሰራ ወጣቱ ሲኒየሩን ይዞ ይወጣል፡፡ ከዛ በኋላ ነው እንዲግህ ቅብብሎሹ ይቀጥላል፡፡ አንዱ ይሄ ነው፡፡ እንግዲህ ይሄንንም በከፊል ሰርተናዋል የሚል ግምት አለኝ፡፡

         ሌላው ይሄንን ወደ ተሻለ ለማድረስ እኛ እኮ ብዙ ነው ዕቅዳችን፡፡ በጣም በርካታ ነገሮች ነው የያዝነው፡፡ ይሄንን  በአንድ ሌሊት እንሰራቸዋለን ማለት አይደለም፡፡ አሁን ስምንት ወር ትልቅ ነገር ይመስላል አይደል? አንድ አትሌት የሚፈራው በአምስት ዓመት ነው፡፡      ሌላው የዚህ  የትሬኒግ ጫና ወዳታች ወርደን ምን እናደርጋለን? ያላችሁ እንደሆነ አሁን እኮ እየተነጋገርን ያላነው ይሄንን የሚዲያ አካላት በተለያየ ክፍለሃገር ቦታ ያሉ በፕሮጀክትም ያሉ ይሰሙታል፡፡ ይሄንን ነው የምናስተላልፈው ማናጀሮችም ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ፕሮጀክቶች ላይ ያሉ ሰዎች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ እዚህም ደግሞ በክለብ የታቀፉ አትሌቶች እንዲሁም በተለያዩ ቦታዎች ያሉ ሊኖሩ ይችላሉ፡፡  በቃ ጫና የግድ ይላል፡፡ ይህንን የማይቋቋም አትሌት ቢኖር በቃ ትሬኒንግ ያንሰናል በቃ የደመደምነው ነው ነገር  ቢኖር ትሬኒግ በሚገባ መሰራት እንዳለበት ነው፡፡ ምንም አልን ምንም እዚህ ሁሉም አስልጠኞች አሉ ከኛ ጋር ለረጅም ጊዜ የቆዩ አሰልጣኞች ናቸው ያውቁታል፡፡ በደንብ ያውቁታል አትሌቶቻችውን ማን ምን ጫና እንደሚችልላቸው ይሄንን ጫና መቋቋም ካልቻለ ምንም ማድረግ አይቸልም፡፡     

      ይሄ ሞፋራህ የተለየ የቴክኖሎጂ አንዳንዱ ነገር በስማ በለው አንዳይሆን፡፡ ከዚህ ልጅ ጋር እኛ ከ2002 ጀምሮ አብረን ስንሮጥ አንድም ግዜ ከፊት አይተነው አናቅም፡፡ ከዛ 2009 ዓ.ም ላይ በጣም ተተኮሰ፡፡ ይሄ ቴክኖሎጂ የምላችሁ ነገር አንዳንድ ግዜ የሚፈቀዱ ነገሮች በጣም ትቂቶች ብቻ ይሆናሉ ለምሳሌ ቅድም ወንድሜ ጠቅሰኸዋል የናይኪ ፕሮጀክት አንዱ ነው፡፡ የናይኪ ፕሮጀክት ዝምብሎ አይደለም ምናልባት ያ ለሱ የተመደበው ገንዘብ ለመላው የኢትዮጵያ አትሌቶች የተመደበ ገንዘብ ሊሆን ትንሽ ነው የሚቀረው፡፡ ያንን መቋቋም ማለት ከባድ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሞፋራህ 600 ሜትር እና ሁለት ዙር  ሲቀር የሚሄደው፡፡

      እሱ የተለየ አትሌት አይደለም፡፡ የተለየው ከጀርባው ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡ ለኛ ከባዶች የነበሩት ያ ቴክኖሎጂ ልጁ ሁለት ዙር አካባቢ ሲቀር እግሩን ብቻ ነው የሚልከው፡፡ በቃ set up ተደርጓል፡፡ ልጆቹ ልክ እየተፍጨረጨሩ መጣን ሲሉ ጥሏቸው ይሄዳል፡፡ ያ ነገር በድግግሞሽ ያየነው ነገር ነው፡፡ እዚህ አሰልጣኞች አሉ፡፡ ሊታዘቡን ይችላሉ፡፡ ቀድመን እንናገር ነበር፡፡ ይሄ ልጅ እንዲህ ከሆነ ያላችሁ ነገር አንድ ብቻ ነው ያም 600 እና 700 ሜትር ሲቀር በተአምር ከፊት ከፊት እንዳይሆን፡፡ ሴክሬቱ እሱ ነበር ያ ከየት የመጣ ነው? እሱ የሰለጠነበት ሁኔታ ነው፡፡     ሌላው የኛ ልጆች የማያገኙት በጣም ብዙ ነገር እሱ ጋር ነበር፡፡ ለምሳሌ አልቲቲውድ ኮንቨርተር የሚባል ነገር፡፡ ለምሳሌ ለንደን ከባህር ጠለል በላይ 150 ወይም ከ200 በላይ አይበልጥም፡፡ ይሄ ሰው ምናልባት እስከ 3000 ባህር ጠለል በላይ ሊተኛ ይችላል፡፡ ይሄንን ቴክኖሎጂ ለምን ተሰጠው? አይባልም፡፡ ይሄንን ምናልባት አሰልጣኞች እና እነ ናይክ ፕሮጀክት ሊመልሱ ይችላሉ፡፡ የመብት ጉዳይ ነው፡፡

       (ከዚህ በታች የተሰጠው ምላሽ በአቶ ዱቤ ጂሎ ነው፡፡)

   መልስ፡- ትንሽ ለመጨመር ብቻ ነው፡፡ የስራ አስፈፃሚ ከመጣ ወዲህ ከዶፒንግ ሌላ በርካታ ስራዎች ተሠርተዋል፡፡ የተሰሩት ስራዎች ከክለቦች ጋር፣ ከክልሎች ጋር፣ ከፕሮጀክቶች ጋር አጠቀላይ የአትሌቲክሱ ሂደት በምን ደረጃ ላይ ይገኛል? በሚል አጠቃላይ የሱፐር ቪዠን ቡድኑ ደግሞ የተወጣጣው ከክለቦች፣ ከክልሎች፣ ከብሔራዊ ቡድን አሠልጣኞችና ከቢሮ የተወጣጣ ሰፊ የሆነ ከ9 ክልሎች እና 2 የከተማ መስተዳድሮች ያሉ ፕሮጀክቶች እያንዳንዱን ጥናት ተደርጎ ያንን ፊድ ባክ ለክልሎቹ ተሰጥቶ ምንድነው ፕሮጀክቱ ላይ ያለው ችግር? ፕሮጀክቱ አሁኑ ያለው ፕሮጀክት አክቲቭ እየሰራ ነወይ? ምንድን ነው ታች ግራውንዱ ላይ ካልሰራን ላይ ብቻ ያለውን እውነታ ቁጭ ብለን ብንጠብቅ ትርጉም አይኖርውም፡፡

      ግራውንዱ ላይ ምንድነው እየተሰራ ያለው?  የሚለውን ነገር እያንዳንዱ ነገር ተለቅሞ ከዛ በኋላ የሚመለከታቸው የባለ ድርሻ አካላት ይሄ ሚዲያ ያውቀዋል፡፡ በእርግጠኛነት የበላይ ባለድርሻ አካለት አጠቃሎ እነሱን ጠርተን በክልሉ  ፕሮጀክቶች ላይ ያሉ ችግሮች ላይ በክለቦች ላይ የክለቦች አደረጃጀት ራሱ አሁን ያሉን ክለቦች አሉ ወይ የሉም ያሉትም ምን ደረጃ ላይ ነው ያሉት? በደንብ ሰፊ ውይይት ካደረግን በኋላ ፊድ ባክ ለክልሎች ተሰጥቶ እንደገና ደግም ያ ተጨምቆ ሁሉ ነገር ተጠናቋል ማለት ነው፡፡  ምክንያቱም ቤዙ ላይ ነው አሁን ፌዴሬሽኑ እየስራ ያለው፡፡ ዶፒንግ አንድ ነገር ሆኖ ማለት ነው፡፡ በከፍተኛ ደረጃ ሰፊ ስራ ተሰርቷል ማለት ነው፡፡ ያ ደግሞ ምክንያቱም ኤሪያዎች ተለይተዋል ከዚህ በፊት ገልጸን ነበር፡፡ ኤሪያዎች የተለዩት ምንድነው? ለምሳሌ ለምንድነው በሩጫ ብቻ በመከካለኛ እና በረጀም ርቀት እስከ ማራቶን ብቻ  ለምንድነው እዛ ላይ የምንቆመው? ለምንስ ደግሞ ለሚቀጥለው ቶኪዮ ኦሎንፒክ እና ለዶሃ ዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከአጭር ርቀት ጀምሮ እስከ ውርወራ ድረስ ምን ማድረግ አለብን? የሚለውን ነገር ስፊ ስራ ተሰርቶ የሌሎችን አገሮችን ተሞክሮ ለወውሰድ ዝግጅቱ ተጠናቆ አሁን ወደ ስራ ለመግባት እየተዘጋጀንበት ያለ ሁኔታ ነው ያለው፡፡ ይሄን በቀላሉ ለመግለፅ ፈልጌ ነው፡፡  ሌላው ሞፋራህ 10ሺ ከሮጠ በኋላ 5ሺ ላይ ምን ማድረግ ለምንድነው መጀመሪያም ያልተጠናው? የሚለውን ነገር በመጀመሪያ ደረጃ ላይ ነው፡፡

      በመጀመሪያ ደረጃ አሰልጣኞቻችን ሞ ፋራህ ምንድነው የሚያደርገው? የሞ ፋራህ የአሯሯጥ ስልት ምንድን ነው ይለዋወጣል፡፡  በየዓመቱ ይለዋወጣል፡፡ ለምሣሌ ቤጀንግ ላይ የነበረው ሩጨ ለንደን ላይ አልድገመውም፡፡ ቤጂንግ ላይ የነበረው ሩጫ 4 ዙር ሲቀር 800 ሜትሩ ላይ ነው የሄደው፡፡ 800 ሜትሩን አንድ ሀምሳ ምናምን ነው የገባው፡፡ መጀመሪያ ሀምሳ ስድስት ሀምሳ አንድ ያንን መቋቋም አልቻሉም፡፡ ይሄን ደግሞ አትሌትቻችን ያንን አድርገው እንዲሰሩ እዚህ ሲመጣ ደግም ሊለውጥ ይችላል የሚል ነገር ሶስት አይነት አስራር ነው አሰልጣኞቻችን ያከናወኑት፡፡ አንደኛ ከአራት ዙር በኋላ ቅድም ሻለቃ እንደገለፀው ምን ማድረግ እንዳለባቸው፤ ሁለተኛ ነገር ደግም የስድስት መቶ ሜትር ላይ ራሳቸውን ጠብቆ መሄድ እንደለባቸው፤ ከዛም ሁለት መቶ ሜትር ከባድ እርምጃ የሚሆነው ያንን ነገር አትሌቶቻችን መቋቋም ይቻላሉ ብለን ነው ሞ ፋራህን የሚቋቋሙት፡፡ እነዚህ ሶስት አትሌቶች ናቸው እንትና አሞት ነው የቀረው፡፡ የአምናው የዛሬ ዓመት የዳይመድ ሊግ አሸናፊ እሱ በህመም ምክንያት ስለቀረ ሶስቱ አትሌቶች ሙክታር አድሪስ ዮሚፍ እና ሰለሞን ባረጋ ስዊድን ከሱ እንደማይተናነሱ ስለታወቀ ኢሄ ይሄን እንደግብ ተቆጥሮ በዚህ መሰረት የተሰጠውን አሳይመንት በስፋት የተወጡበት ነው ፡፡           

     ሁለተኛ ነገር ደግሞ አትሌቱ ደግሞ ለምሳሌ ዙር ሄደ ሰፒድ ይችላል፡፡ አስር ሺ ሜትሩ ላይ አይታችሁ እንደሆነ አብዘኛው የዙር አትሌቶች ናቸው፡፡ ፌስ ፌስ ማለት ሰፒድም ይችላል ስፒድ ደግሞ ገና ለምሳሌ አዳዲስ እና የኖሩ አትሌቶች ስለሆኑ ዙሩን  የማክረር ዙሩን ደግሞ በተቻለ መጠን የማክረር እና በተቻለ መጠን ሜዳሊያ ውስጥ ለመግባት የተደረገው ድርጊት ነው፡፡ ምክንያቱም አይታችሁ እንደሆነ ትንሽ ፈጣን ቢዘገይ የተወሰኑ አንድ እና ሁለት ልጆች ናቸው፡፡ እነሱም ያን ያህል ይሄ ነው ብለን የምንለው አይደለምና በዚህ ነው፡፡ እነሱም ደግሞ ሊያሸንፉን የቻሉት የአስር ሺ ሜትሮቹ ኢንዱራንስ አትሌቶች ናቸው፡፡ ታግለዋል ግን ኢሄም ወደፊት የሚስተካከል ይሆናል፡፡

   (ከታች ያለውን  ቀሪ መልስ የሰጠው የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት ሀይሌ ገብረሥላሴ ነው፡፡)

        እርምጃን በተመለከተ ሁለት አትሌቶች አያልነሽ ደጀኔ እና አስካለ ድንቄሳ ለንደን ላይ ቀርተዋል፡፡ ያው የቀሩበት ምክንያት እንደሚታወቀው ይሄንን እድል አናገኝም በማለት እዚህ ለንደን መጥተን ከሚል አንጻር እንጂ  ሌላ ምንም እንትን እንደሌለ እኔ ምንም አልጠራጠርም፡፡ እንዲሁም ባልጠይቃቸውም ከዚህ የተለየ ነገር ስላልሆነ ነው፡፡ ያው ትንሽ በተለይ በተለይ ቅር ያለኝ ሌሎች እነዚህ ልጆች ተወዳድረው ቢጠፉ ምንም ማለት አይደለም፡፡ ግን ሳይውዳድሩ ነገም ውለው አድረው ተመልሰው የሚመጡበት ሀገር ነች፡፡ ኢትዮጵያን ወክለው ሄዱ ግን ሳይወዳደሩ መሄድ ኦፍ ኮርስ አትሌት ይጥፋ አልልም፡፡ ግን እንደው አትሊስት ትንሽ እሱን ሁላችንንም አበሳጭቷል፡፡ ይሄንን ለማለት ስላልተመለሰ ብዬ ነው፡፡ (ሀይሌ ለተጨማሪ መልስ የሰጠበት ክፍል ነው)    

      (ምክትል ፕሬዝዳንቱ ገብረእግዚአብሔር ገብረማሪያም የሰጠው ምላሽ)

         መልስ፡- እንግዲህ በዓለም ሻምፒዮና ላይ ቡድናችን ላይ የታዩ እኔ እንግዲህ አምስት የዓለም ሻምፒዮና ላይ ተካፍያለሁና በነዛ አምስት የዓለም ሻምፒዮናዎች በመካፈል ያገኘሁት ነገር አለ፡፡ የዓለም ሻምፒዮና ዝግጅቱም ሌላም ሌላም ነገሮች ወደ አትሌቶቻችን ግን ስመለስ እኔ እውነት ለመናገር ትውልድ የነበረው ጄኔሬሽን እና የአሁኑ ጄኔሬሽን የራሱ የሆነ ልዩነት አለው፡፡ ያ የአስተሳሰብ ልዩነት ነው፡፡ የብቃት ልዩነት ነው፡፡ እነዚህ ልዩነቶች አትሌቶቻችን ላይ በሰፊው ተሰራጭተዋል፡፡            አትሌቶቻችን አማካሪ አላቸው፤ የማናጀር አማካሪ አላቸው፤ የጓደኛ አማካሪ አላቸው፤ እንዲሁም አሰልጣኛችን በአግባቡ አለመቀበል ፌዴሬሽኑን በአግባቡ አለመቀበል አላቸው፡፡ ስለዚህ በብዛት የሚያምኑትን በብዛት የሚቀበሉት ከጎናቸው ያለ አማካሪን ነውና ምናልባት ይሄንን አስተሳሰብ መቀየር እንዳለባቸው ብዙ ስራ እንደሚጠበቅና ምናልባት መስራት አለብን፡፡ ለወደፊት ብለን የሚል ነገር ይኖራል፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን አትሌቱን ለመቆጣጠር አሁን እነዚህ አስተሳሰቦች፣ እነዚህ አማካሪዎች፣ እነዚህ ደጋፊዎች የምንላቸው መደገፍ ይችላሉ፤ ማማከር ይችላሉ፤ ግን ሀገር በሚባልበት ወይም ብሄራዊ ቡድን በሚባልበት ካምፕ በሚባልበት ግን እነዚህ ሰዎች መጠጋት እንደሌለባቸው ከብዙ ሀገሮች ተሞክሮ አንፃር አሜሪካ ብንል ኬኒያ ብንል ሌሎች ሀገሮች ብንል እንግሊዝም ብንል የናሽናል ቲም አባል ከሆንክ መኪናህን ጥለህ ቤትህን ጥለህ ያማረ ቤት ይኖርሃል ያማረ መኪና ይኖርሃል ፌዴሬሽኑ በሚያዘጋጀው ካምፕ መታቀፍ መቻል አለብህ፡፡  ስለዚህ ለዚህ አንዱ የብሄራዊ ቡድን ህግ ወይም ደግሞ የካምፕ ህግ ፌዴሬሽኑ ጀምሮታል፡፡ ካምፕ ሲገባ  ትሬኒግ ባግባቡ መጠቀም በጋራ መኖር እንዳለባቸው በጋራ መብላት እንዳለባቸው የሚያስረዳ በአትሌቶችም በአስልጣኞች  በየተለያዩ ሙያተኞችም የተዘጋጀ አለ፡፡ አንድ የካምፕ መቆጣጣሪያ ደንብ እየተዘጋጀ ነው፡፡

               ስለዚህ ለወደፊቱ በዚህ መልኩ እናደርገዋለን ብዬ አስባለሁ፡፡ ምናልባት ግን አንድ የአስር ሺ ላይ እኔም ጠቀስ ማድረግ የምፈልገው አስር ሺ እውነት ለመናገር አትሌቶቻችን ከጠበቅነው በላይ በጣም የሚችሉትን ሁሉ ተጠቅመው ሮጠዋል፡፡

              ሞ ፋራህ ሁለት ነገር ነው፡፡ አስር ሺ ሜትሩን አንዱም ሞ ፋራህ ፊኒሺንግ ስላለው አንድም ዙር ላይ ላይሄድላችሁ ይችላል፡፡ በጣም ቢቀዘቅዝ እንኳን እናንተ ሞ ፋራህን ስለማትችሉት በፊኒሽግ ከሰድስት እስከ አምስት ዙር ሲቀር ወጥታችሁ የቻላችሁትን ያክል ሞክሩ ብለናል፡፡ ሁለተኛው ስትራቴጂ ኬንያውያንና ዩጋንዳውያን በሞፋራህ በጣም ሰለሚናደዱ ፊኒሺንጉ ስለሚያስፈራቸው ሊያፈጥኑት ይችላሉ፡፡ስለዚህ ሞፋራህ እደርስባቸዋለሁ ብሎ ሊቀር ይችላል ስለዚህ ሞ ፋራህ ፍጥነቱን ቀንሶ ሊቀር ይችላል፡፡ ስለዚህ እነሱን እየተከተላችሁ በመሃል ሁኑ የሚል ነበር፡፡  ስለዚህ ሁለተኛው ሲስተም ሰራ፡፡ አከረሩት ተጠጋ ይዘው ሄዱ እስከ መጨረሻው ድረስ ሮጡ በመጨረሻ በሚችሉት መምራት ጀመሩ፡፡ ሶስት ዙር ሲቀር ማለት ነው ይሄ እንግዲህ በኛ አትሌቶች አቅም የሰራነው እና በኛ አትሌቶች አቅም መሆን አለበት ብለን የወሰድነው ሲስተም ነው፡፡

          ሌላው እንግዲህ አሁንም ይሄ የዓለም ሻምፒዮና እውነት ለመናገር አትሌቶቻችን ላይ ደግመን ደግመን አትሌቶቻችን በምንሰጣቸው አሰልጣኞች በሚቀመጥ መመሪያ በሚቀመጥ ስርአት ማመን መቻል አለባቸው፡፡ ይሄንን ስንተማመን እና ወደነበረው መንፈስ ስንመለስ ነው እሱ ብቻ ሳይሆን ትልቁ ከቴክኖሎጂ ጋር መገናኘቱ ምንም እንኳን የሚጠላ ባይሆንም እያንዳንዱ አትሌት ማማሟቂያ ቦታ እንኳን አትሊስት ቴክኖሎጂውን ባግባቡ የማይጠቀምበት ሁኔታ አለ፡፡ ስለዚህ እነዚህን ሁሉ በስርአት እና በደንብ መቀበል መቻል አለበት፡፡ የኮንሰንትሬሽን እኮ አመለካከትን ጉልበትን ሁሉ ያሰንፍሃል፡፡ እነዚህን ሁሉ ለማስተካከል ቀጣይ የሚሰሩ ስራዎች አሉ፡፡    

              ጥያቄ፡- አምስት ሺ ሜትር ላይ ሞ ፋራህን ለማሸነፍ በመከራችሁት ልክ አልማዝ አያና አምስት ሺ ሜትር ላይ እድትሰራ ያደረጋጅሁት ነገር ምድን ነው? ምናልባት አቶ ዱቤ ለንደን እያሉ የሰጡት አስተያየት ነበር የሪዮ አሎንፒክ አይነት ሩጫ እንደሆነ ቅድሚያ መገመት ችያለሁ፡፡ እንደምትሸነፍም አውቅ ነበር በማለት የሰጡት ሃሳብ ጋዜጣ ላይ ወጥቶ አይቻለሁ፡፡ እሱን ነገር ቀድሞ ማስተካከል አይቻልም ወይ?

        ጥያቄ፡- ባል እና አሰልጣኝ ሊለያዩ ይገባል የሚል ሃሳብ ወጥቷል እና እሱ ትንሽ ግልጽ አልሆነም ምናልባት በዚህ ጫና ምክንያት ያጣነው ውጤት አለወይ?            ጥያቄ፡- ስለሁለቱ የጠፉ ልጆች ያልከው ሀይሌ እኔ ያልተዋጠልኝ  ነገር አለ፡፡ ብዙ ጊዜ አትሌቶቻችን ሲጠፋ የሚያነሱት አንተ እንዳልከው አንዱ ኢኮኖሚ ጥያቄ ሊሆን ይችላል፡፡ ሁለተኛው ፖለቲካ ነው፤  ሶስተኛው ግን ብዙ ግዜ አትሌቶች ሲጠፉ  ጫና ተደርጎብናል ነው  ይሄም ከዚህ በፊት  ቀነኒሳና መሰረት ወደድል ከመጡ እና ጡንቻቸውን ካበረቱ በኋላ ብዙ የተደረገባቸው በደል እንዳለ በተለያየ ሚዲያ ላይ ተናግረዋል፡፡ እናንተም ወርዳችሁ ይሄ አመራረጡ ትክክል ነው ወይ? ከአሠልጣኞች ጋር ያለው ከዚህ በፊት ትክክል ባይሆንም አንድ አሠልጣኝም እንደተደበደ አይተናል እና ብዙ ጫናዎች አሉ፡፡ ብዙ ነገሮች የሚባሉ አሉ አቶ ዱቤ የበለጠ ያውቃሉ ከሳቸው ጋር ብዙ እሰጣ እገባዎች ነበሩና ይሄንን ለመፍታት ምን ጥረት አድርጋችኋል?

     ጥያቄ፡- ሀይሌ እና ገብሬ ሌሎች አትሌቶች ወደዚህ እንድትመጡ ሚዲያው ከፍተኛ ጫና አድርጓል በባለሙያዎች እስኪ ይመራ እና  ይሞከር በሚል ነው በዚህም በጠቅላላ ጉባኤው ላይ ከተቋማት ብቻ የተወከለ ሚዲያ መገኘት አለበት ተብሎ ብዙ ጋዜጠኞች ታግደዋል፡፡ አስታውሳለሁ  የተቋም ደብዳቤ አስገብተንም ከበር ተመልሰናል፡፡ እናንተም ኢንቨስተር ስለሆናችሁ የራሳችሁም ስራ የሚወጥራችሁ ናችሁ፡፡ ሀይሌን ለማግኘት ለውጪ ለሀገር ውስጥ ለቤተሰብ የተለያየ ስልክ አለው የሚባል ነገር አለ፡፡ ከሚዲያውም ጋር ከተወሰኑት ጋር ነው ግንኙነት ያለህ በርግጥ ከሁለት መቶ ሚዲያ ጋር መገናኘት ከባድ ነው ግን የገቡ አንዳንድ ጥያቄዎች ከጽ/ቤት ወደ ስራ አስፈጻሚ ከስራ አስጻሚ ወደ ጽ/ቤት የሚያመላልስ ነገር አለ፡፡ እናንተ ጽ/ቤቱ ስራውን እንዲወጣ ሙሉ ለሙሉ ሃላፊነት ሰጥታችሁ እንዲወጣ አድርጋቸኋል ወይ?

         እኛ የአትሌቶች ችግር የለብንም ከበቆጂም አልፎ ወደሌሎች ክልሎች እየሄደ ነው አልማዝ አያና ለዚህ ምስክር ነች ችግራችን ማኔጅመንት ነው ከበፊት ጀምሮ ለማኔጅመንት አልታደልንም እናንተ እንድትመጡ ብዙ ጥረት ተደርጓል፡፡ ከመጣችሁ በኋላ ግን ሃይሌ ተበሣጭተህ ተማረህ ስትናገር አይቼሀለሁ፡፡ በዚህ ስምንት ወር በጣም የገዘፈ ውጤት ባንጠብቅም አሁን ስናየው ግን ምንም የተለየ ነገር አይታይም እና እናንተ የተሻለ ነገር እንሰራለን ነው የምትሉት ወይስ ምን አስባችኋል?         መቼም ሀይሌ ሩጫ ብዙም አቋርጠህ ወጥተህ አታውቅም እና ይሄንን አቋርጠህ ትወጣለህ ወይ?  

                  በቀጣይ ለነዚህ እና ለሌሎች ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶችን ከድምጽ መቅረጻችን ላይ ገልብጠን እናቀርብላችኋለን