እንደ ጎርጎርሲያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2007 በእንግሊዙ ክለብ አርሰናል ስፖንሰር የተጀመረው የኤምሬትስ ዋንጫ ዘንድሮ 10ኛ አመቱ ላይ ደርሷል፡፡

ወድድሩ በ4 ክለቦች መካከል ለ2 ቀናቶች ሲከናወን እያንዳንዱ ክለብ ሁለት ጨዋታዎችን የማድረግ ግዴታ ሲኖርበት ጨዋታውን ከማሸነፍ በተጨማሪ የተሻለ ጎል ማስቆጠር ደግሞ የዉድድሩ ሻምፒዮን ያደርገዋል፡፡

በታላቁ ኤምሬትስ ስታዲዬም እስካሁን ድረስ ዉድድሩ 8 ጊዜ ተከናዉኖ መድፈኞቹ 4 ጊዜ ሻምፒዮን በመሆን ቀዳሚ ናቸዉ፡፡ ሀምቡርግ፣ ኒዮርክ ሬድ ቡል፣ ጋላታሳራይና ቫሌንሻ ደግሞ የኤምሬትስ ዋንጫን አንዳንድ ጊዜ ማንሳት ችለዋል፡፡

ዉድድሩ በ2012 እና በ2016 በተለያዩ ምክንያቶች ያልተካሄደ ሲሆን ዘንድሮ ለ9ኛ ጊዜ ከደቂቃዎች በኃላ በ4 ቡድኖች መካከል በይፋ ይጀምራል፡፡ የእንግሊዙ አርሰናል የጀርመኑ ሌፒዚግ የስፔኑ ሲቪያና የፖርችጋሉ ቤኔፊካ ደግሞ ተሳታፊ ቡድኖች ናቸዉ፡፡
በዚህ መሠረትም
10:00 ሌፒዚንግ ከሲቪያ
12:20 አርሰናል ከቤኔፊካ ጨዋታቸዉን ያደርጋሉ፡፡
የኤምሬትስ ካፕ በነገዉ እለት ፍፃሜዉን ያገኛል፡፡